Training in Scientific Computing for female Graduates of Maths and Statistics at HU.
Training in Scientific Computing for female Graduates of Maths and Statistics at HU.
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀምን ተከትሎ ባገኘው ውጤትና በ2016 በጀት አመት መሪ እቅዱ ላይ አጠቃላይ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።
የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዘለቀ አርፍጮ የመድረኩን መዘጋጀት አስፈላጊነት አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ኮሌጁ በ2016 ዓ.ም እቅዶቹን በተሻለ አፈጻጸም ለማከናወን ይችል ዘንድ ተጠንቶ በተዘጋጀው መሪ እቅድ ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን እንደ ግብአት ለመቀበልና ተገቢውን የክለሳ ስራ ለመስራት መሆኑን ተናግረዋል። ዲኑ አክለውም የሚደረግበት ኮሌጁ በ2015 ዓ.ም በነበረው የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተሰራው የደንበኞች የእርካታ ደረጃ ጥናት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበትና ከሪፖርቱ የተገኙ ግብረ መልሶችን በመመልከት በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ: ተገልጋይ ደንበኞችንም በላቀ ደረጃ ለማገልገል ጠንካራ ስራዎች እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የማ/ሳ/ስ/ሰ ኮሌጅ የእቅድና መረጃ አስተዳደር አስተባባሪ ዶ/ር ማሙዬ በልሁ በበኩላቸው ውይይቱ በዚህ መልክ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መካሄዱ ባለሙያው በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ከማስቻሉም በተጨማሪ ለተግባዊነቱና ውጤታማነቱ በተሻለ ተነሳሽነት እንዲሰራ እንደሚያስችለው ተናግረዋል። ባለፈው አመት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል ብሎም ክፍተት የታየባቸውን እቅዶች ደግሞ በጥልቀት ገምግሞ ተገቢውን ማሻሻያ በማድረግ በተያዘው የበጀት አመት አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም የዕለቱ ተሳታፊዎች ቃል መግባታቸውን ዶ/ር ማሙዬ ጨምረው ገልጸዋል።
በማጠቃለያውም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ በ2015 ዓ.ም ሁሉም ኮሌጆች በተሳተፉበት የአፈጻጸም ግምገማ ውጤት የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ሶስተኛ ደረጃን ያገኘበት ድል በዕለቱ በጋራ ተከብሯል። በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዳይሬክቶሬቶች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ድጋፍ ሰጪ አካላት ተሳትፈውበታል።
A Team from MoE holds discussion with HU officials on e-SHE project implementation.
A Consultative workshop held on SRH Health Services.
የበይነ መረብ ትምህርት (e-learning) ስልጠና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ።
አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶች በሀዩ ኮ/ስ/ሪፈራል ሆስፒታል።
Page 21 of 100
Contact Us
Registrar Contact