የትምህርት ሚኒስቴር ሱፐርቪዥንና ድጋፍ

የትምህርት ሚኒስቴር ሱፐርቪዥንና ድጋፍ ቡድን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ምልከታና ውይይት።

በትምህርት ሚኒስቴር የስኮላርሺፕና አለምአቀፋዊነት ዴስክ ኃላፊው ዶ/ር ኢዶሳ ተርፋሳ የተመራው የሱፐርቪዥን ቡድን ከጥቅምት 19-21 ቀን 2016 ዓም ሲያካሂድ የቆየውን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም አጠቃላይ የእቅድ አፈጻጸም ግምገማና አካላዊ ምልከታ አጠናቋል::

በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተካሄደው የአስተዳደር ሰራተኞችና የተማሪ ተወካዮች ውይይት ላይ የቡድኑ መሪ ዶ/ር ኢዶሳ እንደገለፁት ትምህርት ሚኒስቴር በየአመቱ የዩኒቨርሲቲዎችን የእቅድ አፈጻጸም ለመገምገም በአካል ተገኝቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንዲሁም የመስክ ምልከታ እንደሚያደርግ ገልጸዋል::

አላማውም ከሚኖረው ውይይትና የመስክ ምልከታ ሊቀጥሉ የሚገቡ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል እንዲሁም ሊሻሻሉ የሚገባቸውን ጉድለቶች ማሻሻል በሚቻልበት አቅጣጫ ላይ የሚገኘው ግብረ-መልስ ለበላይ አመራሮች ይሰጣል ብለዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፕላንና ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ቡርቃ በበኩላቸው ከትምህርት ሚኒስቴር የመጡት ባለሙያዎች ያለፈውን አመት እቅድ አፈጻጸም በመገምገም በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት ዩኒቨርሲቲው ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በመለየት የሚሰጡት ውጤት በቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ የሚገቡ ተግባራትን ለመለየት ስለሚያስችል ይህ ምልከታ መካሄዱ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

የሱፐርዚ ዥን ቡድኑ በቀጣይነት ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ የኮሌጅ ዲኖች እና ዳይሬክተሮች ጋር የተወያየ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው አገልግሎቶች ላይ የመስክ ምልከታ አድርጎ ያገኘውን ውጤትም ለሀላፊዎቹ በማቅረብ ግልፅ ውይይት በማድረግ ስራውን አጠናቋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et