የአገልጋይነት ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

የአገልጋይነት ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል በ2015 ጳጉሜ 1 ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የአገልጋይነት ቀን አስመልክቶ በሀዋሳ ከተማ በተመረጡ 5 ቦታዎች ላይ ነፃ የጤና ምርመራ ዘመቻ እያካሄደ ይገኛል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሩ ክፍሌ በዘመቻ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተዉ እንደገለፁት ሆስፒታሉ ሁልጊዜም ማህበረሰቡን በቅንነትና በትጋት የሚያገለግል መሆኑን ጠቅሰው የአገልጋይነት ቀንን በማስመልከት ደግሞ ከጠዋቱ 1:30 ጀምሮ ነፃ የጤና ምርመራ ዘመቻ በሆስፒታሉ ግቢና በሀዋሳ ከተማ በተመረጡ ቦታዎች ላይ ማለትም በሪፈራል ሰርክል፣ በሀዋሳ ከተማ ማረሚያ ቤት፣ በአሮጌዉ መናሃሪያ እና በአሮጌዉ ገበያ እየሰጠ እንደሚገኝ አብራርተዋል::

ዶ/ር ክብሩ አክለዉም የጤና ምርመራ እና ልየታዉ በደም ግፊት፣ ስኳር፣ ኤች.አይ.ቪ፣ የቆዳና አባላዘር፣ የአንገት በላይ፣ የአይን ምርመራ፣ የክብደትና ቁመት ልኬት፣ እንዲሁም የቲቢ ምርመራ እንደሆነ ገልፀው ምርመራዉ አቅመ ደካሞችን ታሳቢ በማድረግ በነፃ እንደሚሰጥ ተናግረዋል:: እንደ ዶ/ር ክብሩ ገለፃ ምርመራና ልየታ የሚደረግባቸው የበሽታ አይነቶች በሕብረተሰቡ ዘንድ ብዙም ትኩረት የማይሰጣቸዉ ነገር ግን ገዳይ በመሆናቸዉ ትኩረት እንደሚገባቸው ጠቁመው ከምርመራዉ ጎን ለጎንም የደም ልገሳ እየተካሄደ እንደሆነ ተናግረዋል::

በቦታዉ በመገኘትም ህክምና እና ምርመራ ከሚደረግላቸው ታካሚዎች ባገኘነዉ መረጃ የዚህ መሰሉ ዘመቻ በጣም አስፈላጊና አቅመ ደካሞችን ከደዌ የሚታደግ በመሆኑ ቀጣይነት ቢኖረዉ መልካም መሆኑን አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et