የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ስልጠና

የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ስልጠና በSTEM ማዕከል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴ/ሽ/ም/ፕ/ፅ/ቤት የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከሲዳማ ክልል ት/ቤቶች ለተመረጡ 160 የ7ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ሳይንስ (STEM) ማዕከል ከነሐሴ 15/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ነሐሴ 30/2015 ዓም ተጠቃሏል።

የም/ቴ/ሽ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዮስ በተማሪዎቹ ሽኝት መርሃግብር ላይ ተገኝተዉ እንደተናገሩት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እያደረገ ያለዉን የለዉጥ ሥራ ለመደገፍ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገዉ ሁሉ በትምህርታቸው ጥሩ ዉጤት ያመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎች ላይ በማሰልጠን፣ በማነቃቃትና የተግባር ሙከራዎችን በማስተማር ላለፉት 15 ቀናት መቆየታቸውን ገልፀዋል:: ም/ፕሬዚደንቱ ለተማሪዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች የነገዉ ትዉልድ ተረካቢዎች በመሆናቸው ትምህርታቸው ላይ ትኩረት በማድረግ ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና ሀገራቸውን የሚለዉጡ ብርቱ ዜጋ እንዲሆኑ አደራ ብለዋል።

የሲዳማ ክልል ት/ቢሮ የሒሳብና ሳይንስ ትምህርቶች ቡድን አስተባባሪ አቶ ቶንቶሻ ቶጋ ከሲዳማ ክልል ካሉ ወረዳዎችና ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ት/ቤቶች ጥሩ ዉጤት ያመጡ፣ ጥሩ ስነ ምግባር ያላቸዉና በሳይንስና ፈጠራ ስራ ላይ ዝንባሌ ያላቸዉ ተማሪዎች ተመርጠዉ ስልጠናዉን እንዲወስዱ መደረጉን ገልፀዉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲም የዚህ መሰሉን ትዉልድን የመደገፍና የማብቃት ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል።

የማዕከሉ ኃላፊና በተፈ/ቀ/ሳ/ኮሌጅ የስታስቲክስ ት/ክፍል መምህር ሄኖክ ዋሪሶ እንደገለፁት ማዕከሉ በክረምት የእረፍት ጊዜ የዚህ አይነት ስልጠናዎችን የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው ወደፊትም ስልጠናዉ የሚቀጥል መሆኑን: በተጨማሪም ክህሎትና የፈጠራ ስራ ዝንባሌ ያላቸዉ ጎበዝ ተማሪዎች ባሉት ቤተ ሙከራዎች ፈጠራዎቻቸዉን እንዲያጎለብቱ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ስልጠናዉን የወሰዱ ተማሪዎችም በተሰጣቸዉ ስልጠናና ተሞክሮ መደሰታቸዉን እና መነቃቃት እንደፈጠረላቸው በሽኝት መርሃግብሩ ላይ ገልፀዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et