የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የእውቅና ሽልማት

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2015 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ኮሌጆች የዋንጫና የእውቅና ሰርተፊኬት ሽልማት ተበረከተ::

በወንዶ ገነት የደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ሲካሄድ በነበረው የሁለት ቀን የውይይት ጉባኤ ማጠቃለያ ባለፈው የበጀት ዓመት በነበራቸው አፈፃፀም ግምገማ መስፈርት የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ኮሌጆችና የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የእውቅና አሰጣጥ መርሃግብር ተካሂዷል:: በውድድሩም የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ: የሀዋሳ ግብርና ኮሌጅ እና የማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል::

ፕሬዚደንቱ ዶ/ር አያኖ በራሶ ሽልማቱን አስመልከቶ ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም ኮሌጆችና የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያስመዘገቡት ውጤት በአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ሥራ አፈፃፀም አንፃር ሲታይ እጅግ አበረታች መሆኑን ገልፀው በበጀት ዓመቱ የነበረባቸውን ተደራራቢ የስራ ጫናዎች ተቋቁመው እጅግ ስኬታማ መሆናቸውን አስምረውበታል:: "ስለሆነም ምንም እንኳን ጤናማ የውድድር መንፈስን ለመፍጠርና ባሉን ጠንካራ ጎኖች ላይ አትኩረን የበለጠ ለመትጋት ብሎም ደከም ባልንባቸው ነጥቦች ላይ ትኩረት ሰጥተን የተሻለ ነገን ለመፍጠር ውድድሩ አስፈላጊ ቢሆንም ዘንድሮ ባሳያችሁት ትጋት ለኔ ሁላችሁም አንደኛ ናችሁ!" ብለዋል:: በመጨረሻም ሁሉም የስራ ክፍሎች የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመጪው ግዜ ከሚጠብቀው ተመራጭና ተወዳዳሪ ራስ ገዝ የምርምር ዩኒቨርሲቲ የመሆን ጉዞ አንፃር አቅደው ያለመታከት የየድርሻቸውን እንዲወጡ አደራ በማለት እና የጉባኤው አስተናጋጅ ለሆነው የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ልባዊ ምስጋና አቅርበው ፕሮግራሙን አጠቃለዋል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et