ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮውን አገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ለመፈተንና ለማስተባበር ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡትን መምህራን በከተማዋ የሚገኙ የመስህብ ቦታዎችን አስጎብኝቷል::
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና አሉሙናይ ጉዳዮች ዳይሬክተርና የኘሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ዮሐናን ዮካሞ በጉብኝት መርሀግብሩ ወቅት እንደገለጹት በሀዋሳ ከተማና በሀገራችን ያሉ ተፈጥሮአዊ ሀብቶችና ፀጋዎችን በተገኘው አጋጣሚ መጎብኘት ብዙ ጠቀሜታ አለው። የዛሬው የጉብኝት አላማም በ2015 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በትምህርት ሚንስቴር ተመድበው የመጡ ምሁራን በተወሰነ ደረጃ የሀዋሳ ከተማንና በከተማው ያሉ ስፍራዎችን እንዲያውቁ ለማድረግ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት የተዘጋጀ የጉብኝት ፕሮግራም ነው ብለዋል፡፡
በጉብኝት መርሀግብሩ ከ400 በላይ መምህራን የተሳተፉ ሲሆን የሐዋሳ ታቦር ተራራና የሲዳማ ህዝብ ዘመን መለወጫ ጨንባላላ የሚከበርበትን ስፍራ (ጉዱማሌን) ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝት ኘሮግራሙ ላይ የተሳታፉ መምህራንና አስተባባሪዎች በሰጡት አሰተያየት በጣም በተጣባበ ጊዜ እንዲህ አይነት የጉብኝት ኘሮግራም በመዘጋጀቱ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።