ለሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝደንት  ጽ/ቤት ለሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ::

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕ/ጽ/ቤት በስሩ ከሚገኙ የስራ ክፍሎች ለተወጣጡ ከ60 በላይ የሚሆኑ የስራ ኃላፊዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች በደንበኞች አያያዝና እርካታ እንዲሁም በጊዜ አጠቃቀም ዙሪያ የአቅም ግንባታና ማነቃቂያ ስልጠና ግንቦት 25/2015 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ሰጥቷል::

የአስ/ል/ም/ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ ስልጠናውን ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ባለፉት ዓመታት ከነበረው አፈፃፀም የተሻሻለና የተሳለጠ አሠራር በመፍጠር የደንበኞችን እርካታ መጨመርና የውስጥ ገቢውን ማጎልበት እንደሚጠበቅበት አውስተው ለዚህም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ረገድ  የሰራተኛውን አቅም ማሳደግ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በአገልግሎት አሰጣጥ የዘመነና ሁሉም የስራ ክፍሎቹ እርስ በእርስ ተናበው እንዲሰሩ ለማድረግ የሚያስችሉ አስፈላጊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ተግባራትም ቀደም ብሎ መከናወናቸውን የገለጹት ምክትል ፕሬዝደንቱ በየደረጃው ለሚገኙት አመራርና ሰራተኞች በመልካም አሰተዳደር ጽንሰ ሀሳቦች፡ የደንበኞች አያያዝና እርካታ፡ የጊዜ አጠቃቀም እና የስሜት ብልህነት በመሳሰሉት ርዕሰ ጉዳዮች ይሄንን መሰል ተከታታይ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን አስረድተዋል::

በዩኒቨርሲቲው የሳይኮሎጅ ትምህርት ክፍል  ተመራማሪ የሆኑት መምህር ሀብተማሪያም ካሳ  ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን በስልጠናው የተሳተፉ ኃላፊዎችና ሰራተኞችም የዚህ አይነት አነቃቂ መድረኮች በየጊዜው ቢኖሩ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠትና የደንበኛን እርካታ ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et