ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ህክምና

ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ህክምና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል።

በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ከሂማሊያን ካታራክት /HCP/ cureBlindness ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነፃ የዓይን ምርመራና የአይን ሞራ ቀዶ ጥገና ሕክምና ከግንቦት 14/2015 ዓ.ም እስከ ግንቦት 19/2015 ዓ.ም ለ775 ታካሚዎች ሰጥቷል::

በኮሌጁ የዓይን ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አርጋው አበራ እንደተናገሩት የቀዶ ህክምና አገልግሎቱ በሞራ ግርዶሽ ምክንያት የተለያዩ የማየት ችግር ያለባቸዉን ታካሚዎች እይታ ለማስተካከል ያለመ ዘመቻ ነዉ፡፡ ለአገልግሎቱ ተደራሽነት ችግሩ ያለባቸው ሰዎች ወደ ሆስፒታሉ እንዲመጡ ቀደም ብሎ በተነገረው ማስታወቂያ ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታካሚ መምጣቱንና አስፈላጊው እርዳታ መሰጠቱንም ለማወቅ ተችሏል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et