ከሚድሮክ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ-ማይኒንግ ክላስተር ጋር በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ የምርምርና የማማከር ስራዎችን በትብብር ለመስራት ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ለምርምር ከተለዩት አንጋፋ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ እንደመሆኑ ከመማር ማስተማር፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎቹ ጎን ለጎን ከሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ካሉ በርካታ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በምርምር፣ በማማከር፣ ስልጠናዎችን በመስጠትና በተለያዩ ስራዎች በትብብር እየሰራ መሆኑን አውስተዋል:: በዛሬው ዕለትም ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ-ማይኒንግ ክላስተር ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ሁለቱ ተቋማት ተቀራርበው በመስራት በዩኒቨርሲቲው ያለውን እውቀት፣ ልምድና የተማረ የሰው ኃይል በመጠቀም እንዲሁም ኢንዱስትሪው ያለውን ሀብት በማጣመር ውጤታማ የትብብር ስራዎችን ከመስራት በዘለለ የዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ -ኢንዱስትሪ ትስስርን ለማጠናከርም እንደሚረዳ ፕሬዚደንቱ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል::

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ በበኩላቸው ስምምነቱን መሰረት በማድረግ ኮሌጁ በባዮሎጂ የትም/ክፍል በሚገኙ ተመራማሪዎችና አማካሪዎች አማካኝነት የስነ-ሕይወት ዘዴዎችን መጠቀም የሚያስችል የምርምር ንድፈ -ሃሳብ በማዘጋጀት በወርቅ ማዕድን ቁፋሮና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ የአካባቢ ብክለት እንዳይፈጠር ለመከላከልና ስነ-ምህዳርን ለመጠበቅ የሚያስችል የምርምር ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ስምምነት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et