በትምህርታቸዉ ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችች ዕዉቅና ተሰጠ

የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በትምህርታቸዉ ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችች ዕዉቅና ሰጠ።

ግንቦት 16/2015 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ  በተካሄደዉ መርሃ ግብር በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ስር ከሚገኙ ስምንት ት/ት ክፍሎች ከ1ኛ-4ኛ  ዓመት የመደበኛ ቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪዎች ባስመዘገቡት ዉጤት መሰረት የተለዩ 27 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲዉ የስራ ሃላፊዎች፣ መምህራንና ተማሪዎች በተገኙበት የዕዉቅና መስጠት መርሃ-ግብር ተካሂዷል፡፡

በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች  ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢንጅነር ፍስሃ ጌታቸዉ ተማሪዎቹን ላስመዘገቡት ዉጤት “እንኳን ደስ አላችሁ!” ካሉ በኃላ ተማሪዎቹ ቀጣዩን ህይወታቸዉን በማቀድ ብቻ ሳይሆን ያቀዱትን እንዲኖሩ አፅንኦት ሰጥተዋል።  ዶ/ር ፍስሃ አክለውም ተማሪዎቹ ከተመረቁ በኋላም ባሉበት ቦታ ሁሉ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አምባሳደር በመሆንና ከዩኒቨርሲቲዉ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት አጠናክረዉ እንዲቀጥሉም አደራ ብለዋል፡፡

የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዘለቀ አርፍጮ መርሃ ግብሩን ማዘጋጀት ያስፈለገበትን ዋና ዓላማ ሲያብራሩ በትምህርታቸዉ የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ለጥረታቸዉ ዕዉቅና ለመስጠትና ሌሎች ተማሪዎችም ፈለጋቸዉን እንዲከተሉ ለማነሳሳት ብሎም ባለድርሻ አካላትን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ለማመስገን እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ዶ/ር ታገሰ ዳንኤል፣ የሬጅስትራርና አልሙናይ ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ክንፈ እንዲሁም የሴ/ህ/ወ/ጉ/ዳ ዳይሬክተር ወ/ሮ ምህረት ገነነ ተማሪዎቹ ያስመዘገቡት ከፍተኛ ዉጤት የትጋታቸዉ ፍሬ፣ የቀጣይ ህይወታቻዉ አቅጣጫ ጠቋሚ መሆኑን ጠቅሰው  የበለጠ መስራትና  ቀጣይነት ያለዉ የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባችዉ ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ   ኮሌጅ ተማሪዎቹን ለማበረታታትና ዕውቅና ለመስጠት ያደረገዉ ጥረትም በበጎ ጅምር የሚታይ መሆኑ ተጠቁሟል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et