በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመስክ ምልከታ አደረጉ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስራ ኃላፊዎች በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመስክ ምልከታ አደረጉ።
 
የ2015 ዓም የበጀት ዓመት የ6 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና ውይይት ላይ የተሳተፉት የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ዛሬ በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢና በመጠናቀቅ ላይ ባለው የካንሰር ህክምና ማዕከል የመስክ ምልከታ አድርገዋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተሩ ዶ/ር አንተነህ ጋዲሳ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት የስድስት ወራት ስራ አፈጻጸም ግምገማው ቀጣይ አካል በሆነው የመስክ ምልከታ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሆስፒታል አገልግሎትና የመማር ማስተማር ዘርፎች የተከናወኑ የእድሳት: የማደራጀትና የማሻሻያ ተግባራት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
 
የኮሌጁ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶ/ር ምህረቱ በላይነህ በበኩላቸው ከቀረበው የስድስት ወራት የእቅድ ክንውን የተገኙ ጠንካራ ጎኖችን ለማስጠበቅና ደካማ አፈጻጸም የታየቸባቸውን ደግሞ ለማሻሻል በተገባው ቃል መሰረት የኮሌጁን አሁናዊ ሁኔታ ለመመልከትና ድጋፍ በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ጉብኝቱ በብዙ እንደሚጠቅም ተናግረዋል።
 
የኮሌጁ ቺፍ ክሊኒካል አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሩ ክፍሌ ደግሞ ኮሌጁ በዋናነት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር፣ ለማህበረሰቡ የጤና አገልግሎትን ማቅረብና የምርምር ስራዎችን መስራት እንደሚገኙበት ገልጸው፤ ላለፉት ስድስት ወራት በእነዚህ ዘርፎች የተከወኑ ተግባራት ከሪፖርት በዘለለ በመሬት ላይ ምን ይመስላሉ የሚለውን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ኃላፊዎች ተገኝተው መመልከታቸው ክፍተት ባለበት ቦታ ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ የተሻለ ግንዛቤ ይሰጣቸዋል ብለዋል።
 
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስቲታል ስራ አስኪያጅ አቶ ዝናው ሳርሞሳ በበኩላቸው ሆስፒታሉ በአሁኑ ወቅት ለብዙ ሚሊዮን የህብረተሰብ ክፍሎች በላቦራቶሪና ዲያግኖስቲክ፣ ድንገተኛና ጽኑ ህሙማን ክፍሎችን ጨምሮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በካንሰር የህክምና ዘርፍ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ስራ አስኪያጁ አክለውም የሆስፒታሉ የላቦራቶሪ አቅም፣ እድሳት ላይ የሚገኘው ሆስፒታል የደረሰበትን ደረጃና የካንሰር ማዕከሉ እየሰጣቸው ያላቸውን አገልግሎቶች ተዘዋውረው የጎበኙት የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች ስለ ሆስፒታሉ አጠቃላይ ሁኔታ የተሻለ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et