በቴክስታይል እና ጋርመንት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ ኤግዚቢሽን ተካሄደ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የቴክስታይል እና ጋርመንት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ ኤግዚቢሽን ተካሄደ።

ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው በዚሁ ኤግዚቢሽን ላይ የኢንስቲትዩቱ አመራሮች፣ የትምህርት ክፍሉ አስተማሪዎች እና ተማሪዎችን ጨምሮ የኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊዎች ነበሩ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሩ ዶ/ር ፋሲካ ቤቴ እንደገለጹት የቴክስታይል እና ጋርመንት ትምህርት ክፍል ጅማሮውን ያደረገው በሀዋሳ ዙሪያ የተመሰረተውን የኢንዱስትሪ ፓርክ መነሻ አድርጎ ለፓርኩ ብቁ የሆኑ ሰራተኞችን ለማቅረብ ታስቦ መሆኑ ታውቋል። የትምህርት ክፍሉ ተማሪዎች በኮቪድ ወርሽኝ ወቅት የአፍ መሸፈኛ ጭምብልን (facemask) በልዩ ፈጠራ በማቅረብ በወቅቱ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው የማይረሳ ተግባር መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ፋሲካ በዛሬው ኤግዚቢሽን የተሳተፉ ከሁለተኛእስከአምስተኛአመትየሚገኙተማሪዎች በቀላል ወጪ የሚሰሩ የጨርቃጨርቅምርቶችን፣ በዘመናዊ መንገድ የሚሰራ የጥጥ መፍተያ ማሽን እና ሌሎች የማህበረሰቡን ሸክም የሚያቀሉ ስራዎችን ማሳየት መቻላቸው የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በማኑፋክቸሪንግ ምህንድስና ፋካልቲ የቴክስታይል እና ጋርመንት ትምህርት ክፍል ኃላፊው መምህር ኤልያስ ለማ በበኩላቸው የኤግዚቢሽኑ ዋና አላማ የትምህርት ክፍል ምርጫ ያላካሄዱት የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች የትምህርት ክፍሉን እንዲተዋወቁትና ምርጫቸው እንዲያደርጉት ብሎም የተቀረው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ ማህበረሰብ ደግሞ ስለትምህርት ክፍሉ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል። አክለውም ቀደም ሲል በዚሁ ትምህርት ክፍል ተምረው የጨረሱ ተማሪዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው እያገለገሉ እንደሚገኙና ሌሎች ደግሞ በአነስተኛ ወጪ የራሳቸውን ምርቶች በማምረት እራሳቸውን ጠቅመው ሀገራቸውንም እያገለገሉ ይገኛሉ ብለዋል። ሴክተሩ በራስ የስራ እድልን ለመፍጠር ብሎም ተቀጥሮ ለመስራትም ሰፊ የስራ እድል ያለበት በመሆኑ ፍላጎቱ ያደረባቸውን ተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተማር የትምህርት ክፍሉ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et