የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት የ2015 ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ስር የሚገኙ የስራ ክፍሎች የ2015 በጀት ዓመቱን ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል፡፡

በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ አዳቶ  በፅ/ቤቱ የሚገኙ የስራ ክፍሎች ዩኒቨርሲቲው የያዘውን ተልዕኮ ግቡን እንዲመታና ውጤታማ እንዲሆን ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ገልፀው እያንዳንዱ የስራ ክፍልም የዩኒቨርሲቲውን እና የፅ/ቤቱን ዕቅድ መነሻ በማድረግ ባቀዱት መሰረት የስድስት ወራት አፈፃፀማቸውን በዚህ መድረክ የምንገመግም ሲሆን ዓላማውም የሚቀርቡ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ድክመት የታየባቸውን ደግሞ በማረም በቀጣይ ውጤታማ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ያስችለናል ብለዋል፡፡

በዕለቱም የስራ ክፍሎቹ አፈፃፀማቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎችም በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ጥያቄና አስተያየቶች ተነስተው በአቅራቢዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመጨረሻም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በስራ ክፍሎቹ የቀረቡ ጠንካራ ጎኖች መቀጠል እንዳለባቸው እንዲሁም ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከዕቅዳቸው በመነሳት  ያልተሰሩ ቁልፍ ተግባራትን በመለየት፣ በታዩ ደካማ ጎኖች እና በተሰጡ ግብረ መልሶች ላይ ትኩረት በመስጠት በቀጣይ ቀሪ ጊዚያቶች ውጤታማ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አሳስበውና የዚህ መሰሉ ውይይትም ቀጣይነት እንደሚኖረው በመግለፅ በተለይ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ፣ የፕሮግራም ኦዲት እና የቤተ-ሙከራ ዕውቅና አሰጣጥ ስራዎችን፣ ዩኒቨርሲቲውን በአለም አቀፍ ደረጃ ከማስተዋወቅና የኦዲት ግኝትን በታቀደው መሰረት ዜሮ ለማድረስ እንዲሁም የመውጫ ፈተናን በተመለከተ የስራ አመራር ሰጥተው ውይይቱ አብቅቷል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et