የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ለድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ለድህረ-ምረቃ የኮሌጁ 2ኛ እና 3ኛ ድግሪ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን ሕግና ደንቦች እንዲሁም መመሪያዎችን አስመልክቶ በጥር 9/2015 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዘለቀ አርፍጮ የዚህ ስልጠና ዓላማ በኮሌጃችን የሚገኙ የ2ኛ እና 3ኛ ድግሪ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን ሕግና ደንቦች እንዲሁም መመሪያዎችን እንዲያውቁት በማድረግ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የሚጠበቅባቸውን ግዴታዎች እንዲወጡ ለማድረግ እና መብቶቻቸውንም አውቀውት እንዲተገብሩት በማገዝ የመማር ማስተማር ሂደቱን ምቹ፣ ሰላማዊና ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል ሲሆን ተማሪዎቹም በእስካሁኑ ቆይታቸው ያጋጠሟቸውና ያልተረዷቸው ነገሮች ካሉ በዚህ መድረክ እንዲጠይቁና የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎቹም በኮሌጁ ድህረ ምረቃ ኃላፊ ዶ/ር ኢዳሶ ሙሉ ገለፃ ከተደረገላቸው በኃላ በአገልግሎት አሰጣጥ እና ትምህርቱ የሚወስደውን ዓመት አስመልክቶ የጠየቋቸው ጥያቄዎችም ከመድረኩ በኮሌጁ ኃላፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et