የማህበረሰብ አገልግሎት  ላይ ተግባር ተኮር ስልጠና ተዘጋጀ

የማህበረሰብ አገልግሎት በእንስሳት መኖ ልማት፣ አያያዝና አመጋገብ ላይ ተግባር ተኮር ስልጠና አዘጋጀ።

ስልጠናው በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽ/ም/ፕ/ፅ/ቤት የማህበረሰብ አገልግሎት ከሕዳር 23 ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ተዘጋጅቷል፡፡ ከሲዳማ ክልል ሰባት ወረዳዎች ለተውጣጡ የመኖ ባለሙያዎችና ልማት ሰራተኞች በእንስሳት መኖ ልማት፣ አያያዝና አመጋገብ ቴክኖሎጂዎችላይ ተግባር ተኮር ስልጠና መሆኑ ተገልጸአል ፡፡

 የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ፍስሃ በስልጠናው መክፈቻ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በደቡብና ሲዳማ ክልሎች በተመረጡ ወረዳዎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችንና የምርምር ውጤቶችን በተመረጡ ዘርፎች ማለትም በሰብል ልማት፣ በእንስሳት እርባታ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በትምህርት፣ በጤናና ስነ-ምግብ እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በማሰራጨትና በማላመድ፣ ቴክኖሎጂን በማሸጋገር፣ ስልጠናና የማማከር አገልግሎት በመስጠት የአካባቢው ማህበረሰብ ኑሮ እንዲሻሻል በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

 አክለውም በዚህ ስልጠናም በእንስሳት መኖ ልማት፣ አያያዝና አመጋገብ ላይ ተግባር ተኮር ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን ባለሙያዎቹ የእንስሳት መኖ በተለይ የሰብል ተረፈ ምርቶችን በማከም እንዴት እንደሚያለሙ፣ የምግብ ይዘታቸውን ሳይለቁ የመፈጨት መጠኑ እና ተበይነቱ እንዲሻሻል እንዲያደርጉ እንዲሁም ለአካባቢያቸው ተስማሚ የሆነውን መኖ እንዲያለሙና እንዲያዘጋጁ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ገልፀው በቀጣይም በተለይ ከፍተኛ የወተት ምርት ባለበት አካባቢ ለሚገኙ ባለሙያዎች መሰል ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡ በስልጠናውም ከ50 በላይ ባለሙያዎች እየተካፈሉ ይገኛል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et