17ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን ተከበረ

17ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በድምቀት ተከበረ።

"ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም" በሚል መሪ ቃል ሕዳር 23/2015ዓ.ም የተከበረው 17ኛውየብሔርብሔረሰቦችቀን በዩኒቨርሲቲው የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተለያዩ ፕሮግራሞች ደምቆ ተካሂዷል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚደንት እና የፕሬዚደንቱ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ታፈሰ ማቴዎስ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድነት ውስጥ ያለውን ልዩነት እውቅና ለመስጠት ከ1998ዓ.ም ጀምሮ ታስቦ የሚውል ቀን ሲሆን በእነዚህ 17 አመታት መልካም የሚባሉ ብዙ ነገሮች የተስተዋሉ ቢሆንም ብዝሀነታችንን ስናከብር የአገራዊ አንድነት ሚዛን በሚፈልገው ደረጃ መጠበቅ ባለመቻሉ ለተለያዩ ችግሮች መዳረጋችንን አንስተዋል።

ም/ፕሬዚደንቱ አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች ብዝሀነትን ለማስተናገድ በሚደረገው ጥረት እያጋጠሙ ባሉ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ላይ የምርምር ስራዎችንም በመስራት በስራ ላይ ላሉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን ማመንጨት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በመጨረሻም ብዝሀነት የሀገራችን ነባራዊ ሀቅ መሆኑን ተቀብለን ከመለያየት ይልቅ አብሮነትን፣ ችግርን ብቻ ከመተንተን መፍትሄ ማፍለቅን፣ አገሬ ለኔ ምን አደረገችልኝ ከማለት እኔ ለሀገሬ ምን አረኩለት የሚሉ ሀሳቦችን በማንገብ ለአገራችን ህብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ መቆም እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ እና ገቨርናንስ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ዲን የሆኑት እና በዕለቱ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት ዶ/ር ንጉሱ በላይ በበኩላቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም ላይ ቀደምት ከሚባሉ እና በርካታ ታሪክ እና የባህል ትሩፋት ካላቸው ሀገሮች መካከል አንዷ መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በርካታ የእምነት፣ የባህልና የአኗኗር ልዩነት ያላቸው ህዝቦች መገኛ ስትሆን ይህ ብዝሀነታችን የውበታችን እና የጥንካሬአችን መገለጫ ሆኖ ለረጅም ጊዜ መቆየቱንና ይህ የብሔርብሔረሰቦች በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ተሰጥቶት መከበሩ ይህን አንድነት ያጠናክረዋል ብለዋል።

ተባባሪ ዲኑ እንደገለጹት ላለፉት በርካታ አመታት ብዝሐነቱ የአንድነት እሴት ከመሆን ይልቅ የልዩነታችን ምንጭ እንዲሆን በርካታ ያልተገቡ ድርጊቶች ሲደረጉ እንደነበርና ሀገሪቱን ወደኃላ ሲጎትቷት የነበረ መሆኑን አስታውሰው በአሁኑ ወቅት ግን ይህንን ለማሻሻል በሕገመንግስቱ አውቅና የተሰጠውን የሕብረብሔራዊ የፌደራል ስርዓትን በሚያንጸባርቅ መልኩ የህዝቦችን እኩል ተሳትፎ እና ውክልና በማረጋገጥ ወደ ብልጽግና የሚደረገውን ጉዞ ማፋጠን እንደሚገባ ተናግረዋል።

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et