ለመምህራን የምክክር መድረክ ተዘጋጀ

የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ስለመውጫ ፈተና፣ ዝግጅትና አሰጣጥ ዙሪያ ለመምህራን የምክክር መድረክ አዘጋጀ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ኮሌጅ በመውጫ ፈተና ዝግጅትና አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት  ከኮሌጁ መምህራን ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ  ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ በስልጠናዉ መክፈቻ ላይ  እንደ ኮሌጅ ከተሰጡን የመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በተጨማሪ እንደ ሀገር በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ከዚህ ዓመት ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲ ተምረው የሚመረቁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውሰድ እንዳለባቸው በተወሰነው መሰረት እኛም በዚህ መድረክ መምህራኖቻችን በስለመውጫ ፈተና ምንነት፣ አሰጣጥ ሂደት፣ የትኩረት አቅጣጫና ይዘት በመሳሰሉት ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በማከልም የመውጫ ፈተናን በሚመለከት መምህራኖቻችን እራሳቸውን እና ተማሪዎቻቸውን በስነ ልቦና፣ በአእምሮና በአካል ዝግጁ በማድረግ ለተማሪዎቻቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት፣ ተማሪዎቻቸው ብቁ የሚሆኑበትን የማስተማር ስልት በመቀየስና አቅጣጫ በማስያዝ፣ ሞዴል ፈተና በማዘጋጀትና በመፈተን እንዲሁም ተጨማሪ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ሁሉም ተማሪዎች ፈተናውን በብቃት እንዲያልፉ ከወዲሁ የበኩላቸውን ዝግጅትና ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ስልጠናዉን ዶ/ር ግርማ ጥላሁን የእንስሳት ሳይንስ የዓሳ ሀብትና እርባታ ት/ክፍል መምህር እና ዶ/ር አለማየሁ ጳውሎስ የኬሚስትሪ ት/ክፍል መምህር የሰጡ ሲሆን በስልጠናው ላይ የተነሱ ነጥቦች ላይ መምህራን ተወያይተዉና ጠቃሚ ሀሳቦች ተንሸራሽረው  ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et