በመውጫ ፈተና ዝግጅትና አሰጣጥ ዙሪያ ተደረገ

የትምህርት ኮሌጅ በመውጫ ፈተና ዝግጅትና አሰጣጥ ዙሪያ ከመምህራን ጋር ውይይት አደረገ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ኮሌጅ በመውጫ ፈተና ዝግጅትና አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት  ከኮሌጁ መምህራን ጋር ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል፡፡

የትምህርት ኮሌጅ ተወካይ ዲን ዶ/ር ደስታ ቃዌቲ ስልጠናውን ሲሰጡ ኮሌጁ እንደሀገርና ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ጥራት ለውጥ ለማምጣት ተግቶ እየሰራ እና በትምህርትም የልዕቀት ማዕከል ባለቤት መሆኑን አውስተው እንደ ኮሌጅ ከተሰጡን የመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በተጨማሪ እንደ ሀገር በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ከዚህ ዓመት ጀምሮ ከዩኒቨርሲቲ ተምረው የሚመረቁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውሰድ እንዳለባቸው በተወሰነው መሰረት እኛም በዚህ መድረክ መምህራኖቻችን በስለመውጫ ፈተና ምንነት፣ አሰጣጥ ሂደት፣ የትኩረት አቅጣጫና ይዘት በመሳሰሉት ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ የተዘጋጀ መድረክ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም የመውጫ ፈተናን በሚመለከት መምህራኖቻችን እራሳቸውን እና ተማሪዎቻቸውን በስነ ልቦና፣ በአእምሮና በአካል ዝግጁ በማድረግ ለተማሪዎቻቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠት፣ ተማሪዎቻቸው ብቁ የሚሆኑበትን የማስተማር ስልት በመቀየስና አቅጣጫ በማስያዝ፣ ሞዴል ፈተና በማዘጋጀትና በመፈተን ሁሉም ተማሪዎች ፈተናውን በብቃት እንዲያልፉ ከወዲሁ የበኩላቸውን ዝግጅትና ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም በስልጠናው ላይ የተነሱ ነጥቦች ላይ መምህራኖች የተወያዩ እና አንዳንድ ሀሳቦችም ላይ እንዲብራራላቸው የጠየቁ ሲሆን ከመድረኩም ምላሽ ተሰጥቶ ወደፊት ወደ ተግባር ሲገባም አፈፃፀም ላይ በሚታዩ ክፍተቶች ላይ በውይይት መፍትሄ ለማበጀት እንደሚሰራ ተገልፆ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et