በመውጫ ፈተና ውጤታማነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተዘጋጀ

የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ በመውጫ ፈተና ውጤታማነት ላይ ያተኮረ ስልጠና አዘጋጀ።
 
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ.ም የኮሌጁ መምህራን እና በተለያየ ደረጃ የሚገኙ አስተዳደር ኃላፊዎች የተሳተፉበትን ለመውጫ ፈተና ውጤታማነት የሚረዳ የዝግጅት ምዕራፍ በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡
 
በስልጠናው ላይ የመክፈቻ  ንግግር ያደረጉት የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ደብረወርቅ ደበበ በኮሌጃችን ላለፉት ዓመታት ለሕግ ተመራቂዎቻችን የመውጫ ፈተና እየሰጠን የቆየን ቢሆንም እንደ ሀገር የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውሰድ እንዳለባቸው በመወሰኑ እኛም እንደ ኮሌጅ ይህንን በመገንዘብ በመውጫ ፈተና ውጤታማነትና የዝግጅት ምዕራፍ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አዘጋጅተናል ብለዋል፡፡ አክለውም ከዚህ በፊት በሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና ዝግጅትና ውጤታማነት ያለንን ልምድ በመጠቀም ተማሪዎች ከመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ ያላቸውን ግንዛቤ በማጥራት በአካል፣ በስነልቦና እና በጥናት እራሳቸውን ዝግጁ እንዲያደርጉ መምህራኖች አመርቂ ስራ መስራት እንዲሁም በትምህርት አሰጣጥም ላይ ተማሪዎቹ በቂውን እውቀት እንዲያገኙ በማድረግና በተለያዩ መለኪያዎችም ተማሪዎቹን መመዘንና ብቁ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
 
በዕለቱ ስልጠናውን የሰጡት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ደርቤ ወርቅነህ እና ዕጩ ዶ/ር ሀብተማሪያም ካሳ ስለ መውጫ ፈተና ምንነት፣ መርሆዎች እና ስለ ተማሪዎች አእምሮ፣ አካልና ስነ ልቦና ዝግጅት ሰፋ ያለ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ከተሳታፊዎች ጋር በተነሱት ነጥቦች ላይም ውይይት ተካሂዷል፡፡
 
 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et