ከገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ጋር ውይይት ተካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ጋር ውይይት አካሄደ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ጋር በዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት መመሪያ ትግበራ እና የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት ያለበትን ነባራዊ ሁኔታን አስመልክቶ ህዳር 5 ቀን 2015 ዓ.ም ውይይት  አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙት የፕላንና ተቋማዊ ለውጥ፣ ግዢና ፋይናንስ፣ የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት፣ የኦዲትና የበጀት ስራ ክፍሎች በተነሱት ርዕሶች ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ያነሱ ሲሆን የባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት እና በተለያዩ ጊዜያቶች የሚወጡ መመሪያዎችን ተፈፃሚ ለማድረግ ስልጠናዎች እንደሚያስፈልጉ አንስተዋል፡፡

የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ታሪኩ አበበ በውይይቱ ወቅት እንዳስታወቁት በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት በታቀደላቸው ግዜና በጀት መከናወናቸውን እና እየተከናወኑ መሆናቸውን የሚመለከታቸው አካላትና ተገልጋዮች እንዲያውቋቸው የግዢ፣ የፋይናንስና ኦዲት ግኝት ስርዓቶች የመረጃ ግልፀኝነት መኖር እንዳለበት አነስተው ይህም ህብረተሰቡ ተሳታፊ እንዲሆን እና በቂ መረጃ እንዲያገኝ በማድረግ አፈፃፀሙም እንዲመረመር እንደሚረዳ የተናገሩ ሲሆን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ደረጃ እየሰራ ያለው ስራዎች መልካም ቢሆኑም የተሰሩ ስራዎች ለሚመለከታቸው አካላት በአግባቡ ተሰንደው መቅረብ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ሌላኛዋ የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ሶስና በየነ በበኩላቸው ከዚህ በፊት የባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በኮቪድ ወረርሽኝና ሌሎች ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሚያደርግ ስልጠና መሰጠት በመጀመሩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠናውን መውሰድ እንደሚችሉ እና የዚህ መሰሉ ውይይት፣ ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et