የምርምር ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ለተመራማሪዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ

የምርምር ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት Kobo Toolbox በሚባል መተግበሪያ ላይ ለተመራማሪዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

በሀገራችን በተልኳቸው የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብለው ከተለዩት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አንዱ እንደመሆኑ ይህንን የተሰጠውን ተልዕኮ ለማጠናከርና ለመተግበር በርካታ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በምርምርና ቴ/ሽ/ም/ፕ/ፅ/ቤት ስር የሚገኘው የምርምር ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ከ9 ኮሌጆችና ከቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለተውጣጡ ከ90 በላይ ተመራማሪዎች Kobo Toolbox የሚባል መተግበሪያ ላይ ከጥቅምት 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

የምርምር ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ራህመቶ አበበ ስልጠናውን ሲከፍቱ በዩኒቨርሲቲው የሚሰሩ ምርምሮች ጥራት እንዲኖራቸውና ተደራሽ እንዲሆኑ በየጊዜው ጥናት ላይ መሰረት በማድረግ የተመራማሪዎቻችንን ክፍተቶች ለመሙላትና አቅማቸውን ለማሳደግ በምርምር ላያ ያተኮሩ የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠን የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም Kobo Toolbox የሚባል መተግበሪያ ላይ በ2015 ዓ.ም የምርምር ምክረ ሃሳቦቻቸው ተቀባይነት ያገኘላቸው ተመራማሪዎቻችን ስልጠና በመስጠት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

ዶ/ር ራህመቶ አክለውም ተመራማሪዎች ይህን መተግበሪያ አጠቃቀሙን ከሰለጠኑ በኃላ   ኮምፒውተራቸውና ስልካቸው ላይ በመጫን በቀላሉ የሚፈልጉትን መረጃ መሰብሰብና መተንተን የሚያስችላቸው ሲሆን  ከዚህ በፊት በሚሰሩት ምርምር ላይ መረጃዎችን ለመሰብሰብ መጠይቆችን በማዘጋጀትና ወረቀት በማባዛት የሚያባክኑትን ገንዘብና ጉልበት የሚያስቀር፣ ተጨማሪ መረጃ የሚሰበስብ፣ የተሰበሰበውን መረጃ ወደ ቋት የሚያስገባና የሚተነትን የሰው ኃይልን የሚያስቀር ከመሆኑም በዘለለ መረጃው ትክክለኛና ከዬት እንደተሰበሰበም ለማወቅ የሚረዳ መሆኑን ገልፀው ስልጠናውን በሶስት ምድብ በመክፈል በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ከዘጠና በላይ ተመራማሪዎች እንዲወስዱት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et