የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ ተአደረገ

የትምህርት ኮሌጅ የ2015 ዓ.ም ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ አደረገ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  የትምህርት ኮሌጅ የ2015 ዓ.ም ሩብ ዓመት አፈፃፀም ላይ በመስከረም ግምገማ ያካሄደ ሲሆን የትምህርት ኮሌጅ ዲን ተወካይና አካዳሚክ ዲን ዶ/ር ደስታ ቃዌቲ ኮሌጁ በሀገር ደረጃ የትምህርት ስርዓት ክለሳ እየተደረገ በመሆኑ በኮሌጁ አስተባባሪነት የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መማሪያ መፅሐፍ የመጨረሻው ክፍል እርማት ተደርጎበት እንዲታተም መላኩን፣ በሰርተፍኬት ደረጃ 1250 ምሩቃንን ማስመረቁን፣ በኮሌጁ የ2015 ዓ.ም ዕቅድ ተዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም አዲስ መሪ ዕቅድ በዩኒቨርስቲ ደረጃ በመዘጋጀቱ መከለሱን እና የክረምት መምህራን የመማር ማስተማር መርሃግብርም በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን ተናግረዋል።

ዶ/ር ደስታ አክለውም በያዝነው ዓመት የድህረ-ምረቃ ተማሪዎችን ለማስተማር እንዲረዳን መግቢያ ፈተና በማዘጋጀትና በመፈተን ብቁ የሆኑትን ለይተን እንዲመዘገቡ ያሳወቅን ሲሆን በሀገር ደረጃ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን የሚፈትኑ መምህራኖችን በመመልመልና ተማሪዎችንም ተቀብለን ለመፈተን ዝግጅት አድርገናል በማለት ገልፀው በቀጣይም የኮሌጁን መምህራን አቅም ለማጎልበት ለስምንት መምህራኖች የሶስተኛ ድግሪ እንዲሁም ለሶስት መምህራኖች  ደግሞ የሁለተኛ ድግሪ እንዲማሩ እየተመቻቸ መሆኑንና የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎች ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን፣ በመማር ማስተማር ላይ ትኩረት በማድረግ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ለመስራት፣ መምህራኖችም በምርምር ስራዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ፣ በ2015ዓ.ም ለሚገቡ መደበኛና የዕረፍት ቀን ተማሪዎችን ማስተማር  ቅድመ ዝግጅት መደረጉን እና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ምጣኔን ለማሳደግ እንዲሁም በዚህ ግምገማ የሚገኙትን ግብዓቶች በመጠቀምና ክፍተቶችን በመለየት  እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱም በኮሌጁ ስር የሚገኙ ክፍሎች ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ላይም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ውይይት ተካሂዶና ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠው ፕሮግራሙ መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et