በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 442 የህክምና እና ጤና ተማሪዎችን መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም አስመረቀ።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ዛሬ ከተመረቁት 422 የህክምና ሳይንስ ተመራቂዎች ውስጥ 157 የሚሆኑት የህክምና ዶክተሮች ሲሆኑ 265 የጤና ባለሙያዎች ናቸው መሆናቸዉን ገልፀዉ ከተመረቁት የህክምና ተማሪዎች መካከል 40 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ኘሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት ከረጅም ጉዞና ዉጣዉረድ በኃላ ዛሬ ለዚህ በመድረሳችሁ “እንኳን ደስ ያላችሁ!” እያልኩኝ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ትምህርት ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ አንዱ የአንዱን ባህል፣ ቋንቋና አኗኗር ጭምር ብዙ ነገሮች እንዳገኛችሁ ተስፋ እያደረኩኝ ትምህርታችሁን በድል በማጠናቀቅ ራሳችሁን፣ ቤተሰቦቻችሁንና ወላጆቻችን እንዲሁም ሃገራችሁን አኩርታችኃልና ልትኮሩ ይገባችኃል ብለዋል።
የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚ/ደኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት ህዝብን ማገልገል ክብር ነዉ፣ ድሃ ወገንን ከስቃይና ከሞት ለመታደግ ማገልገል ደግሞ ድርብ ክብር ሲሆን የጤናና ህክምና ሙያ የተከበረ ሙያ ነዉና ሙያዉ እንደተከበረ ለማቆየት የህክምና ስነምግባር በመላበስ ማህበረሰቡን በተነሳሽነትና በርህራሄ ማገልገል ይጠበቅባችኃል፤ ይህ ደግሞ ዛሬ እዚህ ቆማችሁ እንደምትምሉት መሃላ ተግባሩ በደቂቃዎች የሚጠናቀቅ ቀላል ነገር ስላልሆነ ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ እንደተመረቃችሁ ሁሉ በተግባራችሁም የምትመረቁ እንድትሆኑም አደራ እላለሁ እያልኩኝ በት/ቤት ያገኛችሁትን እዉቀትና ክህሎት በመጠቀም ብቁ ማህበረሰብ አገልጋይ፣ አስተማሪና ተመራማሪ እንዲሁም ለጤናና ህክምና ሙያተኞች አርአያ ለመሆን እንደምትተጉ አደራ እላለሁኝ ብለዋል።