ለተማሪዎች የመማሪያ ግብዓቶች ድጋፍ ተደረገ

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ግብዓቶች ድጋፍ አደረገ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ በደን አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚገኙ 200 አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል፡፡

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል በቀለ ንግግር ሲያደርጉ ኮሌጃችን ከዚህ በፊት ማህበረሰቡን ለመደገፍ በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በኮሌጃችን በሚገኘው ReREd ፕሮጀክት አማካኝነት ለተማሪዎች የመማሪያ ድጋፎችን ስናደርግ ተማሪዎችም  ጠንክራችሁና በርትታችሁ እንድትማሩ አደራ እያልኩኝ  እኛም መሰል ድጋፎችን ወደፊት ለማድረግ ፍቃደኞች መሆናችንን እገልፃለሁኝ ብለዋል፡፡

የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን እና የReREd ፕሮጀክት ኃላፊ ዶ/ር ሺመልስ ንጋቱ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ የኮሌጁ ተማሪዎችን ለመደገፍ የፅዳት ዕቃ፣ ለሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን፣ አቅም ለሌላቸው የኪስ ገንዘብ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ እና በኮሌጁ እየተቋቋመ ለሚገኘው የሕፃናት ማቆያም የተለያዩ እቃዎችን እየደገፈ መሆኑን ገልፀው በዛሬው ዕለትም አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ግብዓቶችን እያበረከትን እንገኛለን ብለዋል፡፡

የወንዶ ገነት ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን ሃይሌ ሲናገሩ ተማሪ የነገ ተስፋና ተረካቢ እንዲሁም ትምህርት ቤት ደግሞ ለሀገር ዕድገትና ብልፅግና መነሻ መሆኑን ኮሌጁ ተረድቶ እየደገፈን በመሆኑ ምስጋናዬን እያቀረብኩኝ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ መምህራኖችና የሚመለከታቸው አካላት ጠንክረን እና ተናበን በመስራት ተማሪዎቻችን ለውጤት እንዲበቁ የበኩላችንን እንድንወጣ አደራ እላለሁኝ ብለዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችም በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውንና በርትተው በመማር ጥሩ ውጤት ለማምጣት እንደሚጥሩ ተናግረዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et