የ2014ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ ተካሄደ

 

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ የ2014 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ግምገማ አካሂዷል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ የ2014 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ አካሂዷል፡፡ የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል በቀለ በዕለቱ ውይይቱን ሲከፍቱ በኮሌጃችን በአካዳሚክ፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በአስተዳደር ዘርፍ በዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ እርምጃዎች በዝርዝር የሚቀርቡ ሲሆን በዕቅዳችን ላይ ተቀምጠው ያላከናወንናቸውን ተግባራት እና ክፍተቶቻችንንም በመለየት በቀጣይ እንድተገብራቸው የዚህ መሰሉ ግምገማ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ዲኑ አክለውም በዚህ ዓመት በርካታ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን የመማር ማስተማሩንና የምርምር ስራዎቻችንን በስኬት የተከናወን  በተለይ በትብብር የፕሮጀክት ስራዎች ስኬታማ ከመሆናቸው በላይ ከኖርዌይና ስውዲን መንግስታት በተገኘው ድጋፍ በታዳሽ ኃይል ላይና መሰረተ-ልማትን የማሟላት እንዲሁም ለመማር ማስተማሩ የሚያግዙ ቁሳቁሶች እንዲሟሉ መደረጉን እና በፋይናንስ አጠቃቀም ዙሪያ የተሻልን የነበር ቢሆንም በመጀመሪያ ድግሪ ተማሪዎች የመዝለቅ ምጣኔ ዝቅተኛ መሆንና ፕሮጀክቶችን ወደ በዘላቂነት እንዲቀጥሉ አለማድረግ ላይ ክፍተቶች ስላሉብን በቀጣይ የተማሪዎች ምደባ ላይ በመስራትና ዝቅተኛ ውጤት ላመጡትም ተጨማሪ የማስተማር ዕገዛ ለማድረግ እና ለመደገፍ እንዲሁም የተፈራረምንባቸውን የተብብር ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ማድረግ ላይ በርትተን እንሰራለን ብለዋል፡፡

የወንዶገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ማኔጂንግ ዳይሬክተርአቶ በላይ በልጉዳ በበኩላቸው የኮሌጁ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ሲገመግም በጥሩ ሁኔታ ያገባደድን ሲሆን ባቀድነው ልክ እንድንሰራ የሸቀጦችና የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ዋጋ ንረት፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ደኖች ጭፍጨፋ፣ የነዳጅ ዋጋ ንረት፣ የተሰብሳቢ ሂሳብ ክምችት መፈጠር፣ የዕቃ አቅርቦት ዕጥረት፣ የመብራት መቆራረጥና የመሳሰሉ ችግሮች ያጋጠሙን ሲሆን ላጋጠሙን ችግሮችም መፍትሔ ለማበጀት ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመወያየት ተጨማሪ በጀት ማስመደብ፣ በደን ውስጥ ከፍተኛ ቁጥጥር ማድረግ፣ የተለያዩ ጥገናዎችን ማድረግ፣ ከግዥና ኤጀንሲ ጋር በመነጋገር የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ግብዓቶች እንዲሟሉ አድርገናል ሲሉ ከገለጹት ባሻገር በቀጣይ ዓመትም የመመገቢያና ማብሰያ አገልግሎቶችን የማዘመን፣ የደህንነት ካሜራ የመትከል  እና የችግኝ ተከላ እና የምርት ማዕከልንም በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራዎች እንደሚሰሩ ጠቁመዋል፡፡

በዕለቱም የዓመቱ አፈፃፀም በዝርዝር ከቀረበ በኃላ በተሳታፊዎች ውይይትና ግምገማ ተደርጎ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et