የ2014ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይትና ግምገማ ማካሄድ ተጀመረ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2014ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይትና ግምገማ ማካሄድ ጀመረ፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2014ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይትና ግምገማ እንዲሁም በ2015 ዓ.ም  መሪ ዕቅድ ላይ ለሁለት ቀናት ማለትም ከሐምሌ 16-17/2014 ዓ.ም ድረስ ውይይትና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይም ምክክር ማካሄድ ጀምሯል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በመክፈቻው ላይ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው በየዓመቱ የሚሰራቸውን ስራዎች ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ነቅሶ በማውጣትና በመፈተሸ መሻሻል ባለባቸው ላይ ጥልቅ ውይይትና ግምገማ በማካሄድ እንዲሁም መልካም ተሞክሮዎችን ደግሞ በማስቀጠል ከዚህ የደረሰ መሆኑን አውስተው ባለፈው 2013 ዓ.ም ሐምሌና ነሃሴ ወራት የትምህርት ጊዜ ሳይቋረጥ በዩኒቨርሲቲው ትምህርት እየተሰጠ በመቆየቱ እና ተደራራቢ ምርቃቶች በመኖራቸው ስራዎች ያለዕረፍት በመሰራታቸው ከፍተኛ ጫና የነበረበት ነበር ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎቹ በተጨማሪ ሀገራዊ ተልዕኮዎችን በመወጣት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የደሞዝ ድጋፍ፣ በጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች ተደጋጋሚ ድጋፍ ከማድረጉ በተጨማሪ በጦርነቱ ለተጎዱ ዩኒቨርሲቲዎች ድጋፍ በማድረግ መልሰው እንዲቋቋሙ ዩኒቨርሲቲው ጥረት ማደረጉን አንስተው በዓመቱ ምንም እንኳን በርካታ ስራዎችን ብንሰራም በጉድለቶቻችን ላይ  ብርቱ ውይይትና ምክክር በማድረግ የምርምር ዩኒቨርሲቲ እንደመሆናችን የተሰጠንን ተልዕኮ ለማሳካት ጥልቅ ውይይት ማድረግ ይኖርብናል በማለት መካከለኛው አመራርም ከከፍተኛ አመራሮች ጋር በግልፅ በመወያየት ለተሻለ ስራ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የመጀመሪያው ቀን የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤቶች ዓመታዊ አፈፃፀማቸውን አቅርበው በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይትና ግምገማ የሚደረግ ሲሆን በቀጣዩ ቀንም የ2015ዓ.ም መሪ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን የኮሌጆችና የኢንስቲትዩውቶች የ2014ዓ.ም ዓመታዊ ምዘና ውጤት ቀርቦ የተሻለ ውጤት ላመጡት ዕውቅና እንደሚሰጥ ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et