ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ23ኛው ዙር ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በ2014 ዓም የትምህርት ዘመን ትምህርታቸውን በብቃት ያጠናቀቁ 4603 ወንዶችና 1421 ሴቶችን በድምሩ 6024 ተማሪዎቹን በደማቅ ስነስርዓት በዋናው ግቢ ስታድየም አስመርቋል::
በዚህ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የተካተቱት የ23ኛው ዙር ተመራቂዎች በመጀመሪያ ዲግሪ: በሁለተኛ ዲግሪ: በሶስተኛ ዲግሪ: በእንስሳት ሕክምና እና በልዩ የመምህራን ትምህርት መስኮች የሰለጠኑ ናቸው::
በምረቃ በዓሉ ላይ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የዩንቨርስቲው ፕሬዚደንት ክቡር ዶ/ር አያኖ በራሶ የዛሬውን ምርቃት ለየት የሚያደርገው ሀገራችን በተለያዩ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ብትፈተንም ተግዳሮቶቹን ሁሉ ተቋቁመን ለዚች ቀን በመድረሳችን ነው ብለዋል:: ፕሬዚዳንቱ አክለውም ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባለው ሰፊ መዋቅር: መሰረተልማትና የሰው ኃይል ታግዞ በመጪው ጊዜ ትኩረቱን ወደ ምርምር: የቴክኖሎጂ ስርፀትና በምርምር የታገዘ የማህበረሰብ አገልግሎት እንደሚያደርግ ተናግረዋል:: በተጨማሪም ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለምርምር ከተለዩት 8 የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች አንዱና አንጋፋው መሆኑን አስታውሰው የዛሬዎቹ ምሩቃንም የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አምባሳደሮች በመሆን በፍቅር: በአንድነትና በወንድማማችነት በፅናት በመቆም በብዙ ተስፋና ተግዳሮት የተከበበችውን አገራችንን ብልፅግናና ብሩህ ነገ የሚያግዙ ኃይሎች እንዲሆኑ የአደራ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል::
የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ለተመራቂዎችና ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በብዙ መልኩ ደግፎ ተማሪዎቹን ለዚህ ክብር ላበቃው የሐዋሳ ዩንቨርስቲ ማህበረሰብና በራሳቸው ድካምና ጥረት ለምራቃ ቀናቸው የደረሱትን የቀኑ ባለቤት የሆኑ ተመራቂዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኃላ ምሩቃን የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል ብሩህ ለማድረግ እንዲተጉ አደራ ብለዋል::
 
በምረቃው ወቅት በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ወንድና ሴት እንዲሁም አካል ጉዳተኛ ተመራቂዎች የወርቅ ሜዳልያና ልዩ ሽልማቶች ከተበረከቱ በኃላ የእንስሳት ህክምና: የሕግ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁሉም ተመራቂዎች የሙያዊ ስነምግባር ቃለ መሃላ እንዲፈፅሙ የተደረገ ሲሆን በዓሉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ተደምድሟል::

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et