በሥራ ፈጠራና ቁጠባ እሳቤዎች ላይ ለወጣቶች ስልጠና ተሰጠ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በሥራ ፈጠራና ቁጠባ እሳቤዎች ላይ ለወጣቶች ስልጠና ሰጠ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር በጫማ ማስዋብ ሥራ ላይ ተደራጅተው እየሠሩ ያሉ ወጣቶች ላይ እንደሚያተኩር ተገልፆአል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ፍስሀ እንደገለጹት ከዚህ ቀደምም በግብርና፣ በጤና፣ በስነ-ምግብ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በፈጠራ ሥራዎችና በሌሎች ተዛማጅ ዘርፎች በርካታ ተግባራት በዳይሬክቶሬቱ ተከናውኗል፡፡ በዛሬውም ስልጠና አምና ሰልጥነው ሥራ ላይ ያሉትና አዳዲስ ሰልጣኞችን ጨምሮ በቁጥር 135 የሚሆኑት የድጋፍ ስልጠናውን ይወስዳሉ ሲሉ በያመቱ ተመሳሳይ ድጋፍ በማድረግ የከተማውንም አስተዳደር የማገዝ ሥራ እንደሚሠሩ ዳይሬክተሩ አክለው ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ እንደገለጹት ይህ ዓይነቱ ተግባርወጣቶችን ጎዳና ላይ ወድቆ ለተለያየ ችግር ከመጋለጥና የማህበረሰቡ ስጋት ከመሆን የሚያድናቸው በመሆኑ የኒቨርሲቲው ከከተማም ውጭ በመድረስ በቁርጠኝነት ይህን መሰል ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ከሰልጣኞቹ አንዳንዶቹ ዩኒቨርሲቲው በሚያደርግላቸው ስልጠናና የማቴሪያል ግብአቶች እንደተጠቀሙበት የተናግሩ ሲሆን በተለይ ስልጠናው የባህሪይ ለውጥ እንዲያመጡ ያገዛቸው በመሆኑ እንደተደሰቱና ዩኒቨርሲቲውንም ማመስገን እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et