ዕጩ ተመራቂ ለማ መገርሳ ለሶስተኛ ድግሪ ማሙያ የምረቃ ዕሁፋቸውን አቀረቡ

ዕጩ ተመራቂ ለማ ረጋሳ ለሶስተኛ ድግሪ ማሙያ የምረቃ ዕሁፋቸውን አቀረቡ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ኮሌጅ የፒ.ኤች.ዲ ተማሪ ዕጩ ተመራቂ ለማ ረጋሳ ለሶስተኛ ድግሪ ማሙያ የሚሆናቸውን በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ላይ ያጋጠሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው ላይ ያተኮረ ጥናት አቅርበዋል፡፡ የጥናቱ ዳራ ያተኮረው በኦሮሚያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ትግበራና ተግዳሮቶች እንዲሁም መፍትሔዎቹ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የትምህርት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አብርሃም ቱሉ በጥናቱ ተመራቂው ያቀረባቸው ነጥቦች የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ከፌደራል ጀምሮ እስከ  ት/ቤት ጥብቅ ክትትል እና ሚስጥራዊነቱን በጠበቀ መልኩ በሁሉም ባለድርሻ አካላት የአፈፃፀም ክፍተት መኖሩን፣ የቴክኖሎጂ መዘመን እና ማህበራዊ ሚዲያው ተማሪዎች ከራሳቸው ይልቅ በሌሎች ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ የስነ-ልቦና እና ስርቆት ችግር እያመጣ መሆኑን እና ተማሪዎች ትምህርትን ከማጥናት ይልቅ የፈተና ኮዶች ላይ ትኩረት በማድረግ ኩረጃ እየተበራከተ መምጣቱን የመለከተ ሲሆን በጥናቱም ተመራቂው ፈተናን በሚመለከት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በርብርብ ከትምህርት ሚኒስቴር እስከ ት/ቤት ድረስ ተጠያቂነት እና ኃላፊነት በሚሰማው መልኩ መከናወን እንዳለበት፣ ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት ልጆቻቸው ስርቆትን የሚጠየፉ እንዲሆኑ የስነ-ምግባር ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው እንዲሁም በፈተና ወቅት ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ወደሚገኙት ማዕከላትና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመጡ በማድረግ ስርቆትን ለማስቀረት በቴክኖሎጂ በመታገዝ መሰራት እንዳለበት እንደ መፍትሔ አቅርበዋል ብለዋል፡፡

ጥናቱን በሀገሪቷ ካሉት ዕውቅ ፕሮፌሰሮች በትምህርት ሙያቸው ከተመራቂው ወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑት ፕ/ር ያለው እንዳወቅ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውጪ ገምጋሚ በመሆን እንዲሁም ፕ/ር ተስፋዬ ሰመላ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ገምጋሚ በመሆን በጥናቱ የታዩ ክፍተቶች ላይ ጥያቄና መልስ እንዲሁም የሰላ ትችት በመስጠት በቀጣይ ወረቀቱ በሚፈለገው ደረጃ ተስተካክሎ እንዲቀርብ በመወሰን ተመራቂው በሶስተኛ ድግሪ በትምህርት ምዘናና ግምገማ ስፔሻላይዝድ በማድረግ በጥሩ ውጤት እንዲጨርስ ወስነዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et