የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ

የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር  እና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ጎበኝተዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትሯ እና የዩኒቨርሲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢንጅነር ፍስሃ ጌታቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ1969ዓ.ም የግብርና ጁኒየር ኮሌጅ በመባል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር ሆኖ እንደተቋቋመና በወቅቱም በአራት የዲፕሎማ ፕሮግራሞች 217 ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩን፣ በ1992ዓ.ም ደግሞ ሶስት ኮሌጆችን ማለትም የግብርና ኮሌጅ፣ የወንዶ ገነት ደን ኮሌጅን እና የዲላ መምህራንና ጤና ሳይንስ ኮሌጅን በመያዝ የደቡብ ዩኒቨርሲቲ ተብሎ የቆየ ሲሆን ከስድስት ዓመት በኃላም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመባል ተቋቁሞ የመማር ማስተማር፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ እና በቅርቡም በተልዕኮ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብለው ከተለዩ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑን ገልፀው በአሁኑ ሰዓት 54 የሶስተኛ ድግሪ፣ 141 የሁለተኛ ድግሪ እና 102 የመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራሞችን በመክፈት ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝ፣ በርካታ ምርምሮች በዩኒቨርሲቲው እና በትብብር ፕሮጀክቶች ድጋፍ እየተሰሩ መሆናቸውን እና ከ60 በላይ የትብብር ፕሮጀክቶችን ከተለያዩ የውጪ ሃገራትና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር እየተሰሩ መሆናቸውን ገለፃ አድረገዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትር ናሲሴ ጫሊ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ እና በቅርቡም የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብሎ እንደመሰየሙ ባሉት እምቅ ሃብቶች ላይ ትኩረት በማድረግ በሀገሪቷ ላይ ያለውን የትምህርት ጥራት ችግር ለመፍታት እንዲሁም በትኩረት ተለይተው በተሰጡት አቅጣጫዎች ላይ ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማካሄድ አመርቂ ውጤት ማምጣት እንዳለበት እንዲሁም በአካባቢው ለሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ በዘርፉ ባለሙያዎችን ማሰልጠን እንዳለበትና ሀዋሳ ከተማም ለቱሪዝም ምቹ በመሆንዋ በዚህ ላይም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትሯ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር ውይይትና ምክክር ከደረጉ በኃላ ዩኒቨርሲቲውን ዞረው በመመልከት ይፋው ጉብኝታቸውን ማጠቃለላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et