በምርምር ፖሊሲ ብሪፍ አዘገጃጀት ላይ ለተመራማሪዎች ስልጠና ተሰጠ

የምርምር ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት በምርምር ፖሊሲ ብሪፍ አዘገጃጀት ላይ ለተመራማሪዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት በምርምር ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት አማካኝነት በዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች ከሚሰሩ ምርምሮች የፖሊሲ ብሪፍ ለማዘጋጀት የሚረዳቸውን የፖሊሲ ብሪፍ አዘገጃጀት ስልጠና  ከሰኔ 8-9/2014 ዓ.ም ለተመራማሪዎች በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ በስልጠናው መክፈቻው ላይ ሲናገሩ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት 46 ዓመታት ለሀገሪቷ ዕድገት አስፈላጊ የሆነውን የሰው ኃይል በማሰልጠን እና በርካታ ምርምሮችን እያበረከተ የሚገኝ ተቋም ሲሆን በተለይ ባለፉት 20 ዓመታት የሰራቸውን ችግር ፈቺ ምርምሮች በመገምገም፣ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ የሰው ኃይል እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታን በማገናዘብ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብለው ከተለዩት አንዱ መሆኑን አውስተው በአሁኑ ሰዓት 132 ምርምሮች እየተሰሩ እና የምርምር ውጤቶችም ተደራሽ እንዲሆኑ ያሉንን የጆርናል ቁጥሮች በማሳደግ የምርምር ውጤቶቹ እንዲታተሙ እየተደረገ ቢሆንም ከአቻ ተቋማት ጋር ሲነፃፀር በቂ ባለመሆኑ አሁንም መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ምርምርን በተመለከተም ዶ/ር ታፈሰ አክለው የምርምር ውጤቶች ጥራት በታተሙበት ቦታ፣ በሚፈጥሩት ተፅዕኖና የማህበረሰቡን ችግር ምን ያህል ለመፍታት ቻሉ በሚሉት መመዘኛዎች መለካት እንደሚቻል አውስተው ተመራማሪዎቻችን የምርምር ውጤቶችን ከማሳተም በዘለለ ከሚጠበቁ ውጤቶች አንዱ ለፖሊሲ አውጪዎችና አዘጋጆች የሚጠቅም ፖሊሲ ብሪፍ ማዘጋጀት አንዱ በመሆኑ በዚህ ስልጠና ያገኛችሁትን ግብዓት በመጠቀም ልክ እንደ ምርምር ውጤቶቹ ህትመት የፖሊሲ ብሪፍ በማዘጋጀቱም ላይ ትኩረት እንድትሰጡ አደራ እያልኩኝ በቀጣይም በተመሳሳይ መልኩ የኢኮኖሚ እና ቴክኖሎጂ ማንዋል አዘገጃጀት ላይ ስልጠና እንደሚሰጥ እና ዩኒቨርሲቲውም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር አንዳርጋቸው ካሳ ስልጠናው ሲሰጡ በየዘርፉ የምንገኝ ተመራማሪዎች ምርምሮችን ከሰራን እና ካሳተምን በኃላ ከመተው ይልቅ ከዚህ በዘለለ ለሀገር ዕድገትና የማህበረሰባችንን ችግሮች እንዲፈቱ ፖሊሲ ብሪፍ በማዘጋጀት በፖሊሲ እና በህግ እንዲካተቱ በማድረግ ተግባራዊ እንዲሆኑ የበኩላችንን መወጣት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et