አውደ ርዕይ ማስጀመሪያ ፎረም ተካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኢንፎ ማይንድ ሶሊውሽንስ ድርጅት ጋር በመሆን የስራ አውደ ርዕይ ማስጀመሪያ ፎረም አካሄደ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመቀጠር ምጣኔ ማጎልበቻ ማዕከል ከኢንፎ ማይንድ ሶሊውሽንስ ድርጅት ጋር በመሆን በሰኔ 7/2014ዓ.ም የስራ አውደ ርዕይ ማስጀመሪያ ፎረም በዋናው ግቢ አካሄደ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ታገሰ ዳንኤል በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን ከሚገኙ አንጋፋ እና የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች  ተብለው ከተለዩት  የኒቨርሲቲዎች አንዱና ሲሆን ብቁና ተወዳዳሪ ምሩቃንን ለማፍራት በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

አክለውም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ ከንድፈ ሃሳብ ስልጠና በተጨማሪ ተማሪዎች ከዚህ ተመርቀው ሲወጡ ተወዳዳሪና ብቁ እንዲሆኑ ተግባር ተኮር ስልጠና ከመስጠት በዘለለ ከስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ጀምሮ የዳሰሳ ጥናት በማድረግና ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር ፍላጎታቸውን በተመለከተ ምክክርና ውይይት የምናደርግ ሲሆን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ተመራቂዎች በቀጣሪ ድርጅቶች የሚጠበቅባቸውን ክህሎቶች እንዲያሟሉ ከደረጃ ዶት ኮም ጋር በመተባበር ተጨማሪ ስልጠናዎች እንዲያገኙ እና ከቀጣሪዎችም ጋር እንዲገናኙ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኢትዮ ጆብስ አገልግሎት ማናጀር ወ/ሮ ኮከብ አየለ ድርጅታችን ኢንፎ ማይንድ ሶሊውሽንስ የደረጃ ዶት ኮም እና የኢትዮ ጆብስ እናት መስሪያ ቤት ሲሆን ደረጃ ዶት ኮም አንዱ የንግድ ክፍል በመሆን ባለፉት አምስት ዓመታት ከሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር እንዲሁም ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመሆን የተመራቂ ተማሪዎችን የቅጥር ብቁነት ለመጨመር አስፈላጊ የሆኑ የግልዊ እና የሙያዊ ስልጠናዎችን እና የተለያዩ የማማከር አገልግሎቶችን በመስጠት ብቁ ሰራተኞችን በማፍራት ለቀጣሪ ድርጅቶች እያቀረበ ይገኛል በማለት ድርጅቱ ከተመሰረተ ጀምሮም ከ100 ሺህ በላይ ተመራቂዎችን በማሰልጠን 60 ሺህ ተመራቂዎችንም የስራ ዕድል እንዲያገኙ ማመቻቸቱን ገልፀዋል፡፡

በፕሮግራሙም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ደረጃ ዶት ኮም እና የተለያዩ ቀጣሪ ድርጅቶች በተመራቂዎች ላይ እየታዩ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት በጋራ እየተደረገ ስላለው ስልጠናዎች ጠቀሜታ፣ በቀጣይ መስተካከል ስላለባቸው ጉዳዮች እንዲሁም ቀጣሪ ድርጅቶች አሁንም በተመራቂዎች ላይ መሰራት አለበት ባሉት ጉዳዮች ላይ ምክክርና ውይይት ተካሂዶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et