ለኢትዮጵያ ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ለኢትዮጵያ ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ  የጂ አይ ኤስ ትምህርት ክፍል ለኢትዮጵያ ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች ከግንቦት15-ሰኔ 6/2014 ድረስ በ Spatial Data Programming in R& python መተግበሪያዎች ላይ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የጂ አይ ኤስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት መ/ር ምህረቱ በርገኔ ስልጠናውን አስመልክቶ ትምህርት ክፍሉ ለኮሌጁ መምህራን እና ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን የዳሰሳ ጥናት በማድረግና የስልጠና ፍላጎት ጥያቄዎችን በመቀበል በሲዳማና ደቡብ ክልሎች እንዲሁም በፊደራል ተቋማት ለሚገኙ ባለሙያዎች በከተማ መሬት አያያዝ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በደን ጥበቃና በመሳሰሉት ርዕሶች ላይ የጂ. አይ. ኤስ ሶፍትዌር መተግበሪያዎችን በመጠቀም እንዴት መተግበር እንደሚቻል ስልጠናዎችን እየሰጠን የምንገኝ ሲሆን በዚህም ስልጠና ከኢንስቲትዩውቱ ጋር በመተባበር ለ20 ባለሙያዎች የመረጃ አያያዝ የሶፍትዌርና መተግበሪያ ስልጠና የሰጠን ሲሆን ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም መረጃን በአግባቡ ለመሰነድና ተደራሽለማድረግ የሚጠቅም እና መረጃውም ለብዙ ግዜ እንዲቆይ በማድረግ በዚህ መረጃ ላይ በመመስረትም ለሚሰሩ ምርምሮች እና ትንተናዎች ለመረጃ ምንጭነት ለመጠቀም እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

መ/ር ምህረቱ አስከትለውም የስልጠናውን አስፈላጊነት ሲገልፁ ስልጠናው ጊዜና ጉልበትን በመቆጠብ አስፈላጊውን መረጃ በተፈለገው ጊዜ ለማግኘት፣ ድግግሞሽን ለማስቀረት እና ትልልቅና ሰፊ መረጃዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማደራጀት ተደራሽ ለመድረግ እንደሚረዳ ገልፀው በቀጣይም የዚህ መሰሉ ስልጠና ፍላጎት ላቀረቡ የክልልና ፌደራል ተቋማት መሰጠት እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ በላይ በልጉዳ በበኩላቸው ኮሌጃችን አንጋፋ እንደመሆኑ መጠን ከመማር ማስተማር፣ ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ላለፉት ዓመታት  ከመስራት በዘለለ በሀገሪቱ ያለውን የሰው ኃይል ለማሳደግና ክፍተቶችን ለመሙላት የዳሰሳ ጥናት በማድረግና የስልጠና ፍላጎት ጥያቄዎችን በመቀበል ረጅምና አጫጭር ስልጠናዎችን እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን የዛሬው ሰልጣኞችም የዛው አንድ አካል ስትሆኑ የስልጠናው ዓላማ ግቡን የሚመታው በስልጠናው ያገኛችሁትን ክህሎትና ዕውቀት በመተግበር የሚፈለግባችሁን ስትወጡ ነውና ወደመጣችሁበት ተቋም ስትመለሱ ተግባራዊ እንድታደርጉት አደራ እላለሁኝ በማለት ስልጠናው እንዲሳካ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡

ስልጣኞችም ላለፉት ቀናት ባገኙት ስልጠና መደሰታቸውን እና ወደፊትም ለሚሰሩት ስራዎች አስፈላጊና ጠቃሚ መሆኑን የገለፁ ሲሆን መሰል ስልጠናዎች በስራ ወቅት የሚገጥሙ የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ስለሚረዳ ቀጣይነት እንዲኖረው አሳስበዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et