በፆታ እኩልነትና በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

ለሲዳማ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት አባላት በፆታ እኩልነትና በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ለሲዳማ ክልል ምክር ቤት አባላት በፆታ እኩልነትና በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ስልጠና ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡

የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ደብረወርቅ ደበበ በመክፈቻው ላይ በስልጠናው ላይ የሴቶችን እኩልነት የሚያሳዩ እና የፖለቲካ ተሳትፎአቸውን የሚያሳድጉ ሃሳቦች ላይ በሳይንስ የተደገፉ ጥናቶችን በማቅረብ በምክር ቤት አባላቶቹ ውይይትና ምክክር እንዲያደረጉበት የሚደረግ ሲሆን ከዚህ ስልጠናም ሰፋ ያለ ልምድን በመቅሰም ሴቶች በፖለቲካው ዘርፍ ተሳትፎ እንዳያደርጉ እንዲሁም ተሳትፎም እያደረጉ ምን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ማነቆዎችና ተግዳሮቶች እየገጠማቸው እንደሆነ ነቅሰው በማውጣት የመፍትሄ መንገዶችን የሚፈትሹበትና በዚህም ስልጠና ላይ የተሳተፉ የምክር ቤት አባላትም በተለይ ሴት አባላቶች ሌሎችን በየደረጃው ያሉ ሴቶችን ለማብቃት ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡

የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ሌክቸረርና አሰልጣኝ መምህርት ማህተመ ፈለቀ በስልጠናው የተካተተው የፆታ እኩልነትና የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ በዓለም ላይ በርካታ ጥያቄዎችን ያስነሳ እና ትኩረት ያገኘ ጉዳይ በመሆኑ እኛም ከራሳችን አካባቢ በመነሳት ለሲዳማ ክልል ምክር ቤት አባላት በዚህ ዙሪያ ስልጠና ብንሰጥ ግቡን ይመታል ብለን በማሰብ ሲሆን እነዚህ አባላት ሕግ አውጪ አካላት በመሆናቸው በጉዳዩ ላይ ግንዛቤ ኖሯቸው በሚያወጡት ሕግ ላይ እንዲያካትቱ ግብዓት ይሆናቸዋል ተብሎም ታምኖበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም የኮሌጁ ዲን የስልጠናውን ምክረ ሃሳብ ያዘጋጁት እና ስልጠናውንም በዋናነት የሚሰጡት በኮሌጁ ገቨርናንስና ልማት ጥናት የሚገኙ  ሴት መምህራን በመሆናቸው  የሴት መምህራን ተሳትፎ በዩኒቨርሲቲው እየጎለበተ እንደመጣ የሚያሳይ ተግባር በመሆኑ ለሌሎች ኮሌጆች አርአያ ይሆናሉ ያሉ ሲሆን ስልጠናውን ላዘጋጁት መምህራን እና ድጋፍ ላደረገላቸው ለዩኒቨርሲቲው ም/ቴ/ሽ/ ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

 

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et