የሕግ ትምህርት ቤት የምስለ ችሎት ውድድር አካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት ብሔራዊ የምስለ ችሎት ውድድር አካሄደ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ የሕግ ትምህርት ቤት ከሲቪል ሶሳይቲ ሪሶርስ ሴንተር (Civil Society Resource Center) ጋር በመተባበር በሃገራችን ከሚገኙ 19 ዩኒቨርሲቲዎች የተወከሉ የሕግ ተማሪዎችን በስደተኛ ሕግ ላይ ብሔራዊ የምስለ ችሎት (Moot Court) የመጨረሻ ዙር ውድድር ከግንቦት5-7/2014 ዓ.ም ድረስ አካሂዷል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ኃላፊና መምህር በኃይሉ እሸቱ እንደተናገሩት ይህ ውድድር ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በንድፈ ሃሳብ የሚያገኙትን ትምህርት በተግባር እንዲያዳብሩት ከማስቻሉም በተጨማሪ ኃሳቦቻቸውን አደራጅተውና አቀናጅተው በማቅረብ ወደ ስራው ዓለም በሚገቡበት ጊዜ የምክንያት ሰዎች እንዲሆኑ የልምድ ልውውጥ የሚያገኙበት መድረክ ከመሆኑም በተጨማሪ ለሕግ ትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የፍትሕ ስርዓቱ በተደላደለ የዕውቀትና ክህሎት መሰረት ላይ እንዲቆም የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል፡፡

አቶ በኃይሉ አክለውም በዚህ ውድድር የተነሳው ርዕስ ዓለማችን እና ሀገራችን እየገጠማት ያለውን ወቅታዊ የስደተኞችን ጉዳይንና መብቶቻቸውን የሚዳስስ የስደተኞች ሕግ ላይ በመሆኑ በጉዳዩ ተማሪዎቹ በጥልቀት ፈትሸው ተገቢውን ዕውቀት እንዲጨብጡ ከማስቻሉም ባሻገር ለህብረተሰቡም የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ለተመራማሪዎችና ባለድርሻ አካላትም በጉዳዩ ላይ ትኩረት እንዲሰጡበት ዕድሉን ይከፍታል ካሉ በኃላ እንደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ዓላማችን ከውድድሩ ጎን ለጎን ተማሪዎቻችን ተወዳድረው ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን በተቻለ መጠን በየዙሩ አዳዲስ ተወዳዳሪዎችን በመተካት ዕድሉን እንዲያገኙና ልምድ እንዲቀስሙ ማስቻል ነው ብለዋል፡፡ የዚህ መሰሉ ውድድር በሕግ ትምህርት ቤት ሲዘጋጅ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን በቀጣይም በያዝነው ዓመት ሰኔ አጋማሽ ላይ አራተኛው ውስጣዊ ውድድር እንደሚካሄድና የሚመለከታቸው አካላትም የበኩላቸውን እንዲወጡ ኃላፊው ገልፀው ለዚህ ውድድር ትብብር ላደረጉ ባለድርሻ አካላትም ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተወዳዳሪዎች መካከል የመጨረሻ ውድድር ተካሂዶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ አርባምንጭ እና አርሲ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ እና ሶስተኛ መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et