ዓመታዊ የምርምር ግምገማ ወርክሾፕ ተካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ጥናት ማዕከል በጋራ ዓመታዊውን የምርምር ግምገማ ወርክሾፕ አካሄዱ።

ሚያዝያ 7 ቀን 2014 ዓ.ም የስምጥ ሸለቆ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ስሜ ማዕከሉ ባለፉት አመታት በአካባቢ ጥበቃ፣ የአየር ንብረት ለውጥና ተጽኖኦዎቹ፣ የመሬት አጠቃቀም እና በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ በርካታ ምርምሮችን እና ስኬታማ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸው መስሪያ ቤቱ ዋና የምርምር ተግባሩን በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች ላይ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ እና በቀጣይም ከኢንዱስትሪ የሚወገዱ ውጋጆች በስነ-ምህዳሩ ላይ ስለሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽዕኖ፣ በምግብ እራስን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ላይ የከተማ ግብርናን ማሳደግ የሚኖረው ድርሻ እና ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎችን መልሰው እንዲያገግሙ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስነ ህይወት ት/ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ግርማ ጥላሁን በበኩላቸው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በስምጥ ሸለቆ አካባቢ እንደመገኘቱ ከስምጥ ሸለቆ ጥናት ማዕከል ጋር በመተባበር በተግባር የሚታዩ ለውጦችን የሀዋሳ ሀይቅን ጨምሮ በሌሎች ሀይቆችም ላይ እንዲታዩ ማድረጉን ተናግረዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህር እና በስምጥ ሸለቆ ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ምህረቱ ዳናንቶ ዛሬ ግምገማ የሚካሄድባቸው ምርምሮች በስምጥ ሸለቆ ስር የሚገኙት የዝዋይ እና የሻላ ሀይቆች ላይ በሰው ልጆች ምክንያት ስለሚደርሱ ተጽዕኖዎች ዋና ትኩረቱን ያደረገ መሆኑን ተናግረው የምርምሮቹ ሂደትና ውጤት በጥልቀት እንደሚታይና ትችት እንዲሁም አስተያየት እንደሚሰጥባቸው፤ በዚህም ምርምሮቹ ያሉበትን ደረጃ ለመረዳትና ድክመታቸውን ለመቅረፍ እንደሚቻል አብራርተዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et