የኢትዮጵያ ወጣቶችና ትምህርት ድጋፍ አገልገሎት የተመሰረተበትን ሁለተኛ ዓመት አከበረ

የኢትዮጵያ ወጣቶችና ትምህርት ድጋፍ አገልገሎት የተመሰረተበትን ሁለተኛ ዓመት በተለያዩ  ፕሮግራሞች አከበረ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና በሌሎች በጎፈቃደኞች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ወጣቶችና ትምህርት ድጋፍ አገልገሎት (YessEthiopia) የተመሰረተበትን ሁለተኛ ዓመት አስመልክቶ በሀዋሳ የሚገኙ አራት የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከላትን የማስተዋወቅ፣ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቁና እየተማሩ የሚገኙ ተማሪዎችን የንግድ ሃሳቦች ውድድር ማካሄድ እና ስኬታማ የንግድ ባለቤቶች እና ወጣቶች የልምምድ ልውውጥ እንዲሁም የማነቃቂያ ንግግር እንዲያደርጉ በየካቲት 12/2014ዓ.ም በግብርና ኮሌጅ ፕሮግራም አዘጋጀ፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶችና ትምህርት ድጋፍ አገልገሎት መስራችና በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አቶ ፍቃዱ ረታ እንደገለፁት የበጎ አድራጎቱ ዋና ዓላማ በሀገሪቱ ላሉ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን የስራ ዕድልን የማመቻቸት እና የትምህርት ጥራትን መደገፍ ሲሆን ባለፉት 2 ዓመታትም በርካቶች ሃሰቦቻችንን በመደገፍና አባል በመሆን በርካታ ስራዎችን በጋራ እየሰራን ሲሆን ዛሬም የንግድ ሃሳቦች ያላቸው ወጣቶች ሃሳቦቻቸውን አቅርበው አሸናፊዎቹን አራት ባንኮች እንዲደግፏቸው ጋብዘናቸው በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የጠብታ አምቡላንስ አገልግሎት ባለቤት አቶ ክብረት አበበ ለወጣቶች የህይወት ልምዳቸውን እና ያሳለፉትን ተሞክሮ እንዲሁም አቶ ጥበቡ አስፋው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ ሰለሆኑ ከህይወት ልምዳቸው በተጨማሪ የዜጎች ግዴታን አስመልክቶ ሀገር የምትለወጠው ሁላችንም የበኩላችንን ስንወጣ ነው በማለት ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፡፡

በመጨረሻም የንግድ ሃሳባቸውን አቅርበው ከአንድ እሰከ ሶስተኛ ለወጡት ተወዳዳሪዎች የተጋበዙት ባንኮች የማበረታቻ ሽልማት ያበረከቱላቸው ሲሆን አሸናፊዎቹንም ለሚያበረታቱ ድርጅቶች የብድር አገልግሎት ከባንኮቹ እንደሚመቻችላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et