የ2014ዓ.ም የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አደረገ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2014ዓ.ም የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አደረገ፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሰባቱም ካምፓሶች በሚገኙት ኮሌጆችና ኢንስትቲዩቶች በ2014ዓ.ም ሊሰሩ ከታቀዱት ውስጥ ባለፉት 6 ወራት በተከናወኑት  የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከጥር19-20/2014ዓ.ም ድረስ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የውይይትና የምክክር መድረክ በአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ እንደገለፁት የ2014ዓ.ም የስራ ሂደት ከሌላ ጊዜ ለየት የሚያደርገው በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ሲንከባለል የመጣ የስራ ጫና ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ መደበኛ የመማር ማስተማሩ ሂደት በክረምትም ጭምር ሲሰራ መቆየቱ እንደሆነ አውስተው በሀገራችን የሰሜኑ ክልል በተከሰተው ጦርነት ወቅታዊ ችግሮች ቢኖሩም የማማር ማስተማር፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎቻችን ሳንስተጓጎል በተሳካ ሁኔታ ግማሽ ዓመቱን ለማገባደድ ችለናል ብለዋል፡፡

ዶ/ር አያኖ አክለውም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ዩኒቨርሲቲውም ሀገር አቀፍ ጥሪዎችን በመቀበል ለመከላከያ ሰራዊት እና በጦርነት ለተፈናቀሉ በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙት ወገኖቻችን የገንዘብ፣ የአይነት፣ የደም እንዲሁም ለተጎዶ ሰራዊቶቻችን በሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት በመስጠት አኩሪ ተግባር መፈፀሙን ተናግረው በዚህ መድረክም የሚቀርቡትን ሪፖርቶች ገምግመን እና ክፍተቶችንም በመፈተሽ ጉድለቶችን በቀጣይ በመሙላት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፕሮግራሙም እስከ ቀጣዩ ቀን ቀጥሎ በነገው ዕለት በቀረቡት የአፈፃፀም ሪፖርቶች ላይ የማጠቃለያ እና በቀጣይ በትኩረት በሚሰሩ ተግባራት ላይ አቅጣጫ ተቀምጦ ፕሮግራሙ እንደሚጠቃለል ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et