የትምህርት ኮሌጅ የ2014ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና ውይይት አካሄደ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ኮሌጅ የ2014ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና ውይይት በጥር 2/2014 ዓ.ም በሻሸመኔ ከተማ አካሄደ፡፡

ዶ/ር አብርሃም ቱሉ የትምህርት ኮሌጅ ዲን በውይይቱ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ሁላችንም እንደምናስታውሰው የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀማችንን ገምግመን መስተካከል ያለባቸውን እርምት አድርገን እንደምንገናኝ የሚታወስ ሲሆን በዚህም የግምገማና የውይይት መድረክ ባቀድነው መሰረት ምን እንደተገበርን በመፈተሸ ጠንካራ ጎኖቻችንን የምናጎለብትበት እንዲሁም የደከምንበትን ደግሞ በማሻሻል በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የሚረዳን የውይይትና ግምገማ መድረክ ነው ብለዋል፡፡

የኮሌጁ ዲን አክለውም እያንዳንዱ ግለሰብ፣ ትምህርት ክፍሎችና ኮሌጆች የሚያስመዘግቡት የተሻለ ድምር ውጤት የዩኒቨርሲቲውን አፈፃፀም ደረጃ እንደሚያሳድጉት አውቀን ሁላችንም ያለንን የስራ ተነሳሽነት በማሳደግ በተሰማራንበት የስራ ድርሻ በጥራትና በጥንቃቄ ስራችንን ከተወጣን የሀገራችንን ዕድገት ለማፋጠን የበኩላችንን እንወጣለን በማለት በኮሌጁ እስከአሁን ያለው በቡድን ተቀናጅቶ የመስራት መንፈስን በማስቀጠል በዚህ መድረክ ተመካክረን በቀጣይ ክፍተታችንን የምንሞላበትና በሞራል የምንሰራበት እንዲሆን ለማሳሰብ እወዳለሁኝ ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙም  ዲኖች፣ የትምህርት ክፍልና የማዕከል ኃላፊዎች  እና የኮሌጅ ማኔጂንግ  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የስድስት ወር አፈፃፀም ሪፖርታቸውንያቀረቡ ሲሆን በቀረቡትም ሰነዶች ላይ ግምገማና ውይይት በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡ 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et