የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በ2014ዓ.ም የስድስት ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ግምገማ አካሄደ

የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በ2014ዓ.ም የስድስት ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ግምገማ አካሄደ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በ2014ዓ.ም የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ግምገማ እና ውይይት በታህሳስ27/2014ዓ.ም በይርጋለም አዋዳ ካምፓስ አካሄደ፡፡

ዶ/ር ወገኔ ማርቆስ የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን በፕሮግራሙ መክፈቻ እንደገለፁት ኮሌጁ ከዚህ በፊት የየስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀሙን በማዘጋጀት እና በመሰነድ ለሚመለከተው አካል የሚልክ ቢሆንም አሁን ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሌጁ ስር ያሉ የስራ ክፍሎች የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀማቸውን እያንዳንዳቸው የሚያቀርቡበት እና የሚገመገሙበት እንዲሁም ጉድለትና ጥንካሬያቸውንም የምንፈትሽበት መድረክ ነው ብለዋል፡፡

የኮሌጁ ዲን አክለውም ከዚህ መድረክ ያገኘነውን ግብዓት በመውሰድ ጉድለቶቻችንን በማረምና በመሸፈን እንዲሁም ጠንካራ ጎኖቻችንም ላይ ተጨማሪ ቀሪ ስራዎችን በማከል በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በርትተን መስራት ይኖርብናል ካሉ በኃላ የምናከናውናቸውም ተግባራት በአግባቡ ተመዝግበውና ተሰንደው በወቅቱ መቅረብ ይኖርባቸዋል በማለት አሳስበዋል፡፡

በዕለቱም በቀረቡ የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶች ላይ ግምገማ፣ውይይት  እንዲሁም ቀጥይ አቅጣጫዎች ተቀምጠው ፕሮግራሙ መጠናቀቁን ከአዘጋጆቹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et