በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ተግባራት የ6 ወራት ሥራ አፈፃጸም ግምገማ ተካሄደ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ተግባራት የ6 ወራት ሥራ አፈፃጸም ግምገማ ተካሄደ  

በዩኒቨርሲቲው የምር/ቴክ/ሽግ/ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ የግምገማ መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው ሪፎርም መነሻ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በምርምር ዩኒቨርሲቲነት ከመመደቡ ወዲህ የምርምር  አሠራሮችን በመከለስና በዕውቀትና በክህሎት የዳበሩና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ተተኪ ምሁራንን ለማፍራት በአዲስ መልክ እንዲዋቀር መደረጉን ገልፀዋል፡፡ በዚህም መሠረት በሁሉም ኮሌጆች የምርምር ሥራዎችን የሚከታተሉና የሚያቀናጁ መዋቅሮች ከመዘርጋታቸውም ባሻገር ውጤታማ የሆኑ ምርምሮች በሼልፍ ላይ እንዳይቆዩ የማድረግና ከተጠቃሚዎች ጋር በወቅቱ የማድረስ ሥራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የግምገማው ዓላማ በበጀት ዓመቱ ለማጠናቀቅ የታቀዱ የምርምር ተግባራት ሳይስተጓጎሉ በተያዘላቸው ጊዜና በጀት እንዲፈፀሙ ለማስቻል ነው፡፡  በዚሁ መሠረት ባለፉት 6 ወራት ጊዜ ውስጥ ለማህበረሰቡ ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎች በግብርና፤ ቴክኖሎጅ፤ ጤና፤ ተፈጥሮ አከባቢ ጥበቃና ትምህርት ዘርፎች ወደ ትግበራ እንዲገቡ መደረጉንና በቀጣይ ወራቶችም ለተጠቃሚዎች የማዳራስና የክትትል ስራዎች በስፋት እንደሚካሄድ ከየኮሌጆቹ ከቀረቡ ሪፖርቶች ለመረዳት ተችሏል፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት ከ60 በላይ የትብብር ፕሮጄክቶች በመካሄድ ላይ የሚገኙ ሲሆን አብዛኛዎቹ ከኖርዌይ፣ ከጀርመን፣ ከኒዘርላንድ፣ ከስዊዲን፣ ከእንግሊዝና ከአሜሪካን ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ጋር በአጋሪነት የሚካሄዱ መሆናቸው  ታውቋል፡፡   

  

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et