ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ አንድነትን በመደገፍ የገንዘብ የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ አደረገ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ አንድነትን በመደገፍ የገንዘብ የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ አደረገ።

ዩኒቨርሲቲው ኢትዮጵያን ለማዳን በሚደረገው ርብርብ የበኩሉን ለመወጣት የራሱን ማህበረሰብ በማነቃነቅ 45 ሚልዮን ብር ለኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስረክቧል። እንዲሁም ከ2 ሚልዮን ብር በላይ ግምት ያለውን የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ በደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት በጦርነቱ ሳቢያ ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖቻችን ለማስረከብ ችሏል፡፡ ይህን ድጋፍ ለማድረግ ሠራተኞች የወር ደመወዛቸውን ከመልቀቅ ባሻገር አልባሳትን ማበርከታቸው ሲታወቅ  ተማሪዎችም በራሳቸው ተነሳሽነት ያላቸውን ሁሉ አቅርበው በከፍተኛ ስሜትና ሞራል ቡድኑን ወደ ቦታው መሸኘታቸው ተገልጾአል፡፡

በርክክቡ ስነስርዓት ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር የተገኙ ሲሆን በስነስርዐቱ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ ህልውናን የማረጋገጥና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን አገራችን ተገዳ በገባችበት ጦርነት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ከዚህ ቀደምም እያደረገ ያለው ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ምስጋናቸውን ቸረው ለመከላከያ አባላት ቤተሰብና ለተፈናቃይ ተጎጂ ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ማድረጉን እንደማያቋርጥ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም የብሔር ብሔረሰቦች ሁለንተናዊ ዕድገት በሚረጋገጥበት ሂደት ሀገራዊ አንድነትን የሚያስጠብቅ እሴት በሚያስቀጥል ተግባር ላይ በማተኮር ዩኒቨርሲቲያችን ጥናትና ምርምር በማካሄድና ብቁና ሀገር ወዳድ ዜጋን ከመቅረጽ አኳያ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ጠንክረን እንሠራለን ብለዋል፡፡ 

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ንቅናቄ በየካምፓሶቹ  የደም ልገሳ እየተካሄደ ያለ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከፊታችን ሰኞ ሕዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዘመቻ መልክ የደም ልገሳ መርሀ ግብር እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et