የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ በተሻሻለ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች ላይ ምክክረ አደረገ

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ በተሻሻለ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች ላይ ምክክረ አደረገ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ኖርሄድ ሪሬድ ፕሮጀክት (NORHED-ReREd project) በተሻሻለ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች ላይ በሲዳማ እና ደቡቡ ክልል ከሚገጁ ባለድርሻ አካላት ጋር በህዳር 11/2014ዓ.ም ምክክረ አደረገ፡፡

ዶ/ር ሽመልስ ንጋቱ በወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ መምህርና የReREd project አስተባባሪ እንደገለጹት የፕሮግራሙ ዓላማ በሲዳማ እና ደቡቡ ክልል ከሚገጁ ሴት ማገዶ ቆጣቢ አምራች እና አከፋፋዮች ጋር ስለማገዶ ቆጣቢ ምድጃ መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች ለመምከር እና በቀጣይም ከሚገኙት ግብዓቶች በመነሳት ክፍተቶችን ለመሙላት እና በጥናት ላይ የተደገፈ  የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚረዳን የምክክር መድረክ ነው ብለዋል፡፡

ዶ/ር ሽመልስ አክለውም የተሻሻለ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ማገዶን ለመቆጠብ፣ የሴቶችን ጤንነት ለመጠበቅ እና የአኗኗር ዘይቤን ለመቀየር ፣ የደን መጨፍጨፍን ለመቀነስ እንዲሁም ከኢኮኖሚው አንጻር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው ባህላዊ የምድጃ አጠቃቀምን ለማስቀረት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርትና ስልጠና በመስጠት እና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ፣ ባለድርሻ አካላት፣ሀገር በቀልና የውጭ ድርጅቶች ድጋፍ በማድረግ፣ ሚዲያውም ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠር አኳያ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ በሲዳማ እና ደቡብ ክልል የሚገኙ የተሻሻለ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራቾችና ሻጮች፣ ሴቶችና ኢነርጂ ማህበር፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ኤጀንሲ፣ አበዳሪ ተቋማት፣ የዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና መምህራኖች እንዲሁም በዘርፉ የሚሰሩ የውጭና ሀገር በቀል ድርጅቶች ተገኝተው በገብያ ጥናትና ማስተዋወቅ፣ የብድር አገልግሎት አሰጣጥ እና በምርቱ ዲዛይን እና ቴክኒካላ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተካሂዶ ውይይቱ መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et