የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት በማካሄድ ከዚህ ቀደም ይደረግ የነበረውን ድጋፍ ለመቀጠል ከስምምነት ላይ ደረሰ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት በማካሄድ ከዚህ ቀደም ይደረግ የነበረውን ድጋፍ ለመቀጠል ከስምምነት ላይ ደረሰ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ መምህራኖች እና የአስተዳደር ሰራተኞች  በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል እየተካሄደ ባለው የህግ ማስከበር እና ኢትዮጵያን ወደ ኃላ ከሚጎትቷት ከሀዲያን አላቆ ለማዳን በሚደረገው ዘመቻ ላይ የበኩላቸውን ለመወጣት እና ሀገሪቷ ያለችበትን ሁኔታ የሚያሳይ የኢትዮጵያ የውስጥ እና የውጪ ጫናዎች ወቅታዊ  ዳሰሳ ጥናት ላይ በህዳር 9/2014ዓ.ም ውይይት አካሄደ፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ሀገራችን በጥቅምት 23 2013ዓ.ም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ወታደራዊ ጥቃት ከተፈጸመብን ዕለት አንስቶ በርካቶች በተለይ በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ ዜጎቻችን ህይወታቸውን እየገበሩ፣ እየተፈናቀሉ እና ለበርካታ ችግሮች እየተጋለጡ ከመሆናቸውም በተጨማሪ በርካታ የውጭ ሀገራትም ሚዲያዎቻቸውን በመጠቀም የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ከፍተውብን የምንገኝበት ወቅት በመሆኑ ከምንጊዜውም በተለየ መልኩ በአንድነት ቆመን በመደጋገፍና ያለንን ጉልበት፣ ሀብትና እውቀት በመጠቀም ሀገራችንን የማዳን ርብርብ የምናደርግበት ጊዜ ላይ ነን ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ከዚህ በፊት የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ደሞዙን ለመከላከያ ከመስጠቱም በተጨማሪ  ዩኒቨርሲቲው በወሎ ለተፈናቀሉት የህብረተሰብ ክፍሎች ቦታው ድረስ በመሄድ የፍራሽ፣አንሶላ፣ ብርድልብስ ኣና መሰል የአይነት ድጋፍ ማበርከቱን ገልጸው ወደፊትም የዚህ መሰሉ ድጋፍ በአፋር ክልልም እንደሚደረግ እና ድጋፉም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

በዕለቱም ዶ/ር ንጉስ በላይ በጥናታዊ ጹሁፋቸው የኢትዮጵያ ፈተና የማለፍ ታሪክ፣ የምዕራባዊያን ጣልቃ ገብነትና ጫናዎች እና ኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ጫናዎችን እንዴት መከላከል እንዳለባት አመላካች ጥናታቸውን ያቀረቡ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም በሚችለው ሁሉ በመረባረብ ምሁራኖቹ በጥናትና በምርምር የሚዲያ ትግል በማድረግ የምዕራባዊያን የሀሰት ፕሮፓጋንዳን ለመመከት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ1 ወር ደመወዝ፣ በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች የደም ልገሳ፣ የአልባሳት እና የአይነት ድጋፎችን ለማድረግ ከስምምነት መደረሱ ታውቋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et