የኢንተርፕራይዝ ልማት የዩኒቨርሲቲውን ገቢ በመስኩ ለማሳደግ የተለየዩ ማሻሻዎችን በማድረግ እየሠራ መሆኑ ተገለፀ

የኢኢንተርፕራይዝ ልማት የዩኒቨርሲቲውን ገቢ በመስኩ ለማሳደግ የተለየዩ ማሻሻዎችን በማድረግ እየሠራ መሆኑ ተገለፀ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እንተርፕራይዝ ገቢ ማመንጫ የወተትና የወተት ተዋጽኦ ማምረቻ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታሪኩ አሸናፊ በእንተርፕራይዙ ዘርፍ ገቢዉን ለማሻሻል እቅድ ይዞ እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ይህንንም ለማከናወን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት በመሥራት የምርቱን ደረጃ ለማሳደግ የምርቱን ጥራትን ማሻሻልና የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂው ያፈራቸውን ማሽኖች ለማስገባት እየሠራ እንደሆነ ተናግረዋል።

እንተርፕራይዙ የሚያመርታቸዉ ምርቶች ፓስቾራይዝድ ወተት፣ አይብ፣ እርጎ፣ ቅቤና ከረን የሚገኝበት ሲሆን በእንተርፕራይዙ የሚመረቱ ምርቶች ተገቢውን የጥራት ደረጃቸዉን እንዲያልፉ ተደርጎ የሚመረት ቢሆንም ሕብረተሰቡ የግንዛቤ እጥረት ስላለውና የሚጠቀሙ አካላት ውስን መሆናቸው ምርቱን በሰፊው ገበያ ላይ ማዋል  አለመቻሉ የገጠመን ችግር ነዉ ብለው ችግሩን ለመቅረፍም ሕብረተሰቡ ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እንሠራለን ብለዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et