ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ አዲስ ለተቀጠሩና በዝዉዉር ለመጡ መምህራን ስልጠና ሰጠ

ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ አዲስ ለተቀጠሩና በዝዉዉር ለመጡ መምህራን ስልጠና ሰጠ።
በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶክተር ታፈሰ ማቴዎስ ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ በሀገራችን ዉስጥ ከሚገኙ አንጋፋ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ እንደሆነ ጠቅሰው ዩኒቨርስቲዉ የሰለጠነ የሰዉ ሀይል በመፍራት ፣ ችግር ፈቺ የሆኑ የተለያዩ ምርምሮችን በማድረግ እንዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን በመስጠት ለአከባቢዉ ማሕበረሰብና ለሀገራዊዉ ሁለንተናዊ እድገት በማምጣት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሆነ ገልፀዋል። በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ አክለዉም የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ አገራዊና ክልላዊ ለዉጡን ተከትሎ በሀገራችን ያሉትን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተልዕኮና በትኩረት ለመለየት በተጠናዉ ጥናት መሠረት በሀገራችን ዉስጥ ወደ ምርምር ዩኒቨርስቲነት ከሚያድጉ ስምንት ዩኒቨርስቲዎች መካከል አንዱ ሆኖ እንደተለየና ዩኒቨርስቲው ካለዉ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፣የምርምር መሰረተ ልማትና የምርምር ህትመቶች ተሞክሮ በመነሳት በግብርናና በስነ ህይወት፣ በጤና፣ በፊዚክስና ሳይንስ ቴክኖሎጂና ምህንድስና፣ እንዲሁም በማሕበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ አያይዘዉ ገልፀዋል።
በተጨማሪም 22 የማሕበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች፣ 10 የቴክኖሎጂ ፈጠራ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንደተደረገና በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርስቲው 64 አለማቀፍ የትብብር ፕሮጀክቶች ያሉት ሲሆን በእነነዚህ ፕሮጀክቶች የተለያዩ የምርምር፣ የማሕበረሰብ አገልግሎቶችና የአቅም ግንባታ ስራዎች በመስራት ላይ እንደሆነ ተነግሯል።
በመጨረሻም ዋናው የሰለጠነው ዓላማ አዲስ የተቀጠሩና በዝዉዉር ከሌላ ዩኒቨርስቲ የመጡ መምህራን ከዩኒቨርሲቲው የምርምር፣ የማሕበረሰብ አገልግሎት፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ እንዲሁም የትብብር ፕሮጀክቶች አሰራር ስርዓቶች ጋር ማስተዋወቅና መምህራን በቂ ግንዛቤ እንዲይዙና በሚቀጥሉት አመታት በዩኒቨርሲቲዉ የምርምር ቴክኖሎጂ ሸግግር ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበርክቱ መደገፍ ነዉ።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et