የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በካይዘን አተገባበርና ተገልጋይ እርካታ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በካይዘን አተገባበርና ተገልጋይ እርካታ ዙሪያ ለኮሌጁ ቤተ-ሙከራ ቴክኒሻኖች እና አስተዳደር ሰራተኞች በዘርፉ እውቅና ባላቸው ባለሙያዎች በመታገዝ ጥቅምት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ከኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ለማሰልጠን ተጋብዘው የመጡት አቶ ቱጁባ ረጋሳ ስለካይዘን ጽንሰ ሀሳብ እና አተገባበር ዙሪያ እንደተናገሩት ካይዘን ብክነትንና ወጪን ለመቀነስ፣ ተነሳሽነትን፣ የትምህርት ጥራትንና የተገልጋይ እርካታን ለመጨመር፣ የተሻለ ምርታማና ውጤታማ ለመሆን እና የአስራር ሂደቶችን ለማዘመን አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ አቶ ቱጁባ ካይዘን አክለውም ካይዘን አሳታፊ፣ ቀጣይነት ያለው፣ ሳይንቲፊክ አቀራረብን የሚከተልና ኢኮኖሚካል በመሆኑ የትምህርትን ጥራት ለማሻሻል እና ብቁ፣ ተፎካካሪና ተመራጫ ምሩቃንን ለማፍራት ተግባራዊ መደረግ እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡
መምህር ሀብታሙ ምህረቱ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ እንደገለጹት የዩኒቨርሲቲያችን ቀዳሚ ተገልጋዮቻችን ተማሪዎቻችን እንደመሆናቸው የተገልይን እርካታ ለመጨመር ከተግባቦት ጀምሮ ያሉትን ችግሮች በመፍታት የአገልግሎት አሰጣጡንም በማዘመን መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በፕሮግራሙም ላይ በተነሱት ርዕሶች ላይ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች ተነስተው እና ውይይት ተካሂዶባቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡