ማህበራዊ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የምክክር አውደ ጥናት አካሄደ

ማህበራዊ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የምክክር አውደ ጥናት አካሄደ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ያካበቱትን ዕውቀት እና ልምድ በመጠቀም እንዴት በሚኖሩበት ህብረተሰብ ውስጥ ተጽዕኖ መፍጠር፣ ለውጥና ልማት ማምጣት እንደሚችሉ ልምድ በሚያካፍሉ ምሁራን በጥቅምት 18/2014ዓ.ም የምክክር አውደ ጥናት አካሄደ፡፡

የምርምርና ቴ/ሽ/ም/ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ  በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በሀገራችን የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብለው ከተለዩ ዩኒቨርቲዎች አንዱ እንደመሆኑ ለሀገራችንና ለአካባቢያችን ማህበረሰብ ጠቀሚና ፋይዳ ያለው ምርምሮችን እያካሄደ ሲሆን በዋናነትም ቴክኖሎጂዎችን በማመንጨት የማህበረሰቡን እግር ለመፍታት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ያሰቀመጠውን ራዕይ ለማሳካትም የሳይንስ ባህልን በየኮሌጆቹ እንዲሰርጽ በማድረግ የምርምር ውጤቶችም በጆርናል ላይ እንዲታተሙ ከመደረጉም በተጨማሪ በርካታ የምርምር ውጤቶች በምሁራኖች በደቡብ ኤፍ.ኤም ሬዲዮ ከምርምር ዓለም በሚል የሚቀርብ ሲሆን የዚህ መሰሉ ልምድ ያላቸውን ምሁራን በመጋበዝ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ማድረግ እና ሴሚናር ማዘጋጀት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና የሶሾሎጂ መምህር ፕ/ር ጌትነት ታደለ በበኩላቸው ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያካበቱትን ዕውቀት፣ ልምድ እና ለወጣሁበት ማህበረሰብ መልሼ ምን ልክፈለው ወይም ልስጠው በሚል ርዕስ ለወጡበት አዘና አካባቢ 48 ሜትር ድልድይ፣ሁለት የመጀመሪያ፣ ሶስት የሁለተኛ ደረጃ እና አንድ የመሰናዶ ትምህርት ቤቶችን እንዴት ማሰራትና ለህብረተሰቡ ማበርከት እንደቻሉ ሰፊ ዳሰሳዊ የህይወት ተሞክሯቸውን አቅርበዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et