የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ቡድን ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ቡድን ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ቡድን “በሥነ-ምግባር አዋጆችና ደንቦች፣ የአመራርነትና ሙያዊ  ሥነ-ምግባር እና ዓለማቀፋዊ  ጸረ-ሙስና እንቅስቃሴን“ በተመለከተ ለኢንስቲትዩቱ ስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በጥቅምት 13/2014ዓ.ም  ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ዶ/ር ፋሲካ ቤተ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት በሀገራችን ዕድገት እንዳይፋጠን እና ድህነት እንዳይጠፋ እንቅፋቶች ከሆኑት መካካል ሙስናና ብልሹ አሰራር ዋነኞቹ መሆናቸውን በመገንዘብ አዲሱ የለውጥ መንግስትም አንዱ የመንግስት  አጀንዳ በማድረግ ትኩረት ሰጥቶ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት የተለያዩ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት ላይ መሆኑን ገልጸው ሙስና ብልሹ አሰራር በሀገራችን ልክ እንደሌሎች ዘርፎች ሁሉ በትምህርት ሴክተሩም ስር እየሰደደ ሲሆን  ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች መብዛት፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ፈተናዎች መዘጋጀታቸው፣ ብቁ ያልሆኑ መምህራንን እና ሰራተኞች ቅጥር፣ አድሎአዊ አሰራር እና ለትምህርት የሚመደበው ከፍተኛ መዋለዕ-ነዋይ ብክነት ላይ የሚታይ በመሆኑ ይህንን በጋራ ለመከላከል እና ለማስቆም ሁላችንም በርትተን መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና መከታተያ ቡድን መሪ ወ/ሮ አመለወርቅ አበበ እንደተናገሩት ክፍሉ ብቻውን  ሰርቶ ለውጥ ስለማያመጣ ሁላችንም በቁርጠኝነትና በመደጋገፍ የጸረ-ሙስ እና ብልሹ አሰራር ትግሉን በመቀላቀል የትውልዱን ስነ-ምግባር  አብረን እንገንባ በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዕለቱም አቶ ዳግም አላምረው የፌደራል ኮሚሽኑ ስልጠና ባለሙያ እና አቶ ከበደ ኩማ የዩኒቨርሲቲው ሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ስልጠና  ሰጥተው እና በቀረበውም ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄዶባቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et