የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በንሳ ዳዬ ካምፓስ ለመጀመሪያ ጊዜ 175 ተማሪዎችን መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም አስመረቀ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በንሳ ዳዬ ካምፓስ ለመጀመሪያ ጊዜ 175 ተማሪዎችን መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም አስመረቀ።

ለዩኒቨርሲቲው 7ኛ ካምፓስ በመሆን ከዋናው ግቢ በ130 ኪ.ሜ በላይ ርቆ በበንሳ ዳዬ ከተማ የተቋቋመው የበንሳ ዳዬ ካምፓስ የመጀመሪያዎቹን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ በስድስት የትምህርት አይነቶች ማለትም በሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ በውጪ ቋንቋና ስነ-ጽሁፍ፣ በእጽዋት ሳይንስና በግብርና እሴት ሰንሰለት አስተዳደር ትምህርት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 175 ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡

ዶ/ር ፍሬው ካሳ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በንሳ ዳዬ ካምፓስ ኤክስኪዩቲብ ዳይሬክተር እንደገለጹት አካባቢው ከዩኒቨርሲቲው ርቆ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ካምፓስ በመከፈቱ የአካባቢው ማህበረሰብ ከመደበኛ የትምህርት ፕሮግራም በተጨማሪ በእረፍትና በማታ የትምህርት መርሃ ግብሮች የትምህርት ዕድል እንዲገኙ እና የስራ ዕድል ያመቻቸላቸው ከመሆኑም በተጨማሪ በተቋሙ በሚደረጉት  የግብርና እና የከርሰ ምድር ሀብት ጥናቶች ውጤት ወደፊት ተጠቃሚ እንደሚሆን ገልጸው የዛሬዎቹ የግቢው የመጀመሪያ ተመራቂዎችም ለዚህ ቀን በመብቃታችሁ እንቋን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እንደገለጹት የዛሪዎቹን ተመራቂዎች ልዩ የሚደርጋቸው እንደ ሌሎቹ የዩኒቨርሲቲያችን ግቢዎች ያልተሟሉና ጋና እየተሟሉ ባሉ መሰረተ ልማቶች ውስጥ በመሆን ያሉትን ችግሮች በመቋቋም ለዚህ ዕለት በመብቃታቸው ሲሆን ተመራቂዎችም የልፋታችሁን ውጤት ለማየት ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል ፡፡

ዶ/ር አያኖ አክለውም የአካባቢው ማህበረሰብ የሚያርስበትን መሬት ትምህርት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ለዩኒቨርሲቲው በማስረከቡ እና ከተማ አስተዳደሩም ላደረጉልን ትብብር ምስጋናዬን እየገለኩኝ የዛሬ ተመራቂዎችም ወደ ስራ ዓለም ስትገቡ የሚያጋጥማችሁን ጊዚያዊ ችግሮችን ወደ መልካም አጋጣሚዎች በመቀየር መፍትሄን በመሻትና በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን እየፈተነ ያለውን የሰላም ዕጦት፣ የጥላቻና አድሎአዊነት አሰራር እንዲሁም የሙስና አስተሳሰብና ተግባርን በመጠየፍ፣ በሀገራዊ አንድነትና በወንድማማችነት በመቆራኘት ያስተማረንን ህብረተሰብ በመርዳት የሀገራችንን ሰላምና ብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ የድርሻችሁን እንድትወጡ አደራ ለማለት እወዳለሁኝ፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et